Addis Ketema Preparatory School

Addis Zemen ጥቅምት26፣2013

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ከተማ መሰናዶት/ቤት የፋይናንስ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር 2013 . በጀት አመት ቁጥር 003/2013 ኣገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

 • 1. ቋሚ እቃ                                                 ሎት 1 የብር መጠን 5000.00
 • 2. የደንብ ልብስ                                             ሎት 2 የብር መጠን 5000.00
 • 3. አላቂ የቢሮ እቃዎች                                     ሎት 3 የብር መጠን 2000.00
 • 4. አላቂ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች                 ሎት 4 የብር መጠን 1000.00
 • 5. አላቂ የጽዳት እቃዎች                                  ሎት 5 የብር መጠን 5000.00
 • 6. የደንብ ልብስ ስፌት                                   ሎት 6 የብር መጠን 2000.00
 • 7. የጽህፈት መሳሪያዎች                                 ሎት 7 የብር መጠን 1000.00

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል

 1.  የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ( ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።ተጫራቾች በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ የስራ ፍቃድ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው
 2. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከነ መጓጓዣው በሚያቀርበው የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ ኣካቶ ማቅረብ አለበት ነጠላ ዋጋውን ማስቀመጥ የሚቻለው የጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ቦታ ብቻ ሲሆን ከኣንድ በላይ ዋጋ የሚያቀርቡበት ካለ ግን ኮፒ በማድረግ ሁለተኛ ገጽ ላይ ጽፈው አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ።
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(CPO)ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳንዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት በኣዲስ ከተማ መሰናዶ /ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
 4. ጨረታ ሰነዱ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በመቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 21 መውሰድ ይኖርባቸዋል
 5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ጨረታ ከመከፈቱ 3 ቀን በፊት አስቀድሞ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ሳምፕል ለማይቀርብባቸው እቃዎች /ቤቱ ድረስ በመምጣት ሳምፕሉን በማየት ማቅረብ ይቻላል።
 6. በእስፔስፊኬሽን መሰረት እና መስሪያ ቤቱ ውስጥ በተቀመጠው ናሙና መሰረት መቶ በማየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሌላው ደግሞ ናሙና ማቅረብ አስቸጋሪ ለሆኑ ወይንም ክብደት ላላቸው እቃዎች የሚወዳደሩበትን እቃ እስፔስፊኬሽን ወይንም ፎቶ ማቅረብ ይችላሉ።
 7. ሌላው ለውድድር ያስገቡትን ናሙና ጨረታው እንደተጠናቀቀ እስከ 6 ወር ድረስ መተው የማይወስዱ ከሆነ ላስገቡት ናሙና የማንጠየቅ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
 8. ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን የምዝገባ ፍቃድ ቫት ቲን የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱና የዋጋ ዝርዝራቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የሁሉንም ሰነድ ኣንድ ኦርጅናልና ኣንድ ኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።ማሳሰቢያ ከተፈቀደው ዋናና ኮፒሰነዶች ቀንሶ ማስገባት አይፈቀድም። በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱ ሙሉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይመለሳል
 9. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ 4.30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቶች ጨረታ ላይ መገኘት ካልቻሉ ህጋዊ ወኪሎቻቸውን መላክ ይችላሉ። ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ መስፈርቱን ካሟሉ ባይገኙም ያልተገኙትም ተጫራቾች ፖስታ ጭምር ይከፈታል።የጨረታ አከፋፈት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዝግ የሆኑ ቀናቶች ከገጠመ በሚቀጥለው ክፍት የስራ ቀን በተቀመጠው ሰኣት ይከፈታል ።ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ወዲያውኑ በመቅረብ እቃውን ከማስገባቱ በፊት የአጠቃላይ ያሸነፈባቸውን እቃ ዋጋ አስር ፐርሰንት ብር (CPO) ከላይ በተጠቀሰው ስም ከባንክ በማሰራት ውል በመዋዋል ያሸነፉባቸውን እቃዎች ግዢ ፈጻሚው መስሪያቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 10. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

አድራሻ አዲስ ከተማ የከፍለሃገር አውቶብስ ተራ አጠገብ የሚገኘው

አዲስ ከተማ መሰናዶ /ቤት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112763811/15/17

በአዲስ ከተማ ክፍስከተማ አስተዳደር

ትምህርት /ቤት አዲስ ከተማ መሰናዶ /ቤት