Addis Ababa City Administration Public Property Procurement and Disposal Agency

Addis Zemen Tir 18, 2013

የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ

የግዥ መስያ ቁጥር: አግንማስ/2013-2015 ማስ/ብግጨ/አግ11/04/2013

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ ለ3 ዓመት የሚቆይ የተሽከርካሪ ጥገና (ጋራዥ) ኣገልግሎት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም አየር ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም፡

  • ጨረታው ከጥር 13/2013 ዓ.ም በኋላ ለተጨማሪ 15(አስራ አምስት) የስራ ቀናት የተራዘመ በመሆኑ መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ሰንጋ ተራ ሰሚገኘው ዩቤክ ኮሜርሻል ሴንተር ህንፃ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 606 በአካል በመቅረብ የማይመለስ 300 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ጨረታው የካቲት 5/2013ዓም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 5፡30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 9ኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡
  • አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557 31-70 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት

ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት