Addis Ababa City Government Public Procurement and Property Disposal Agency

Addis Zemen Hidar 15, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ /ቤቶች የሆኑ

 • የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣
 • ንብረቶች  (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣
 • የተለያዩ የግንባታ እቃዎችና መለዋወጫዎች፤
 • የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችና በርሜሎች) እና
 • ቁርጥራጭ  ብረታ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡
 1. ተጫራቾች ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ዮቤክ የንግድ ማዕከል ሕንፃ ላይ በሚገኘዉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 606 በመምጣት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ ሌሎችን ብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣  ከነመዳሪዎች፣ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችና መለዋወጫዎች፤ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችና በርሜሎች) እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሠነድ ለተሽከርካሪዎ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለሌሎች ንብረቶች ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እና  ለቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለዉ ማስታወቂያዉ በአዲስ መን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
 2.  በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለዉ አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልጸዉ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 708 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ተገኝተው ማስገባት አለባቸው።
 3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል በሰጡትዋጋ እንዲሁም በነጠላና  በጥቅል የሰጡት የዋጋ መካከል ልዩነት ካለው አገልግሎታችን ከፍተኛውን ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል፡፡
 4. ተጫራቾች ትከከለኛ አድራሻቸዉንና ስማቸዉን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸዉ ላይ መፈረም አለባቸዉ፡፡
 5.  ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ማለትም  የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች የአንዱን /ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው።
 6.  ተጫራቾች ለሚዙት ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%) እና ለሌሎች ንብረቶች 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት  ማስወገድ አገልግሎት ስም አሠርተዉ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ዉስጥ ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲፒኦ  በአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
 7. የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ሰዓት ተጫራቾች  ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 9 ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸዉ የጨረታዉን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
 8.  የተሽከርካሪዎችና ሌሎች ንብረቶች የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተገለጸላቸዉ 7 የሥራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ ክፍያ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያዉን በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡  
 9. የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች አሸናፊዎች ያሸነፉበትን  ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች 7 የሥራ ቀናት የሙሉ ክፍያውን 75% ክፍያ በጥሬ ገንዘብ በአገልግሎታችን ሂሳብ ቁጥር በማስገባት ደረሰኝ ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን፤ ቀሪውን 25% ደግሞ በአገልግሎቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አስይዘው ካቀረቡ በኋላ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በአንድ ወር ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
 10.  በተሽከርካሪው የነበረው ማንኛውም እዳና የስም ዝውውር  ወጪ በአሸናፊ ተጫራች ይሸፈናል፡፡
 11.  ለጨረታ የቀረቡት የሞተር ሳይክሎች በከተማ አስተዳደር የስም ዝውውር ማድረግ የተከለከለ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች ይህንን አውቆ መወዳደር የሚችል ሲሆን፤ ከዚህ አልፎ ለሚመጣውችግር አገልግሎቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
 12. የተሽከርካሪዎችና ንብረቶችን የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች  ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለዉ በመክፈል ክፍያውን ከፈፀሙ በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ፡፡
 13. አንድ ተጫራች ከአንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ መደብ ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡
 14. አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪና ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም::
 15. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፣
 16. የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ስጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡
 17.  ማንኛዉም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከጨረታዉ መዉጣት ወይም የሰጠዉን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
 18. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች  ተቀባይነት የላቸውም፡፡
 19. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡– 011-557-86-71 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ።
 20. አገልግሎታችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመንግሥት ግዥና ንብረት

ማስወገድ አገልግሎት