Addis Ababa Kaliti Customs Branch Office

Addis Zemen Tahsas 27, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2013

የቅ/ጽ/ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት

 • ሎት 1. የአደጋ መከላከያ፣ የጤና መጠበቂያ፤
 • ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
 • ሎት 3 ቋሚ እቃዎች/ማሽነሪዎች/፣ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፈርኒቸር/፤ መጋረጃና ምንጣፍ ግዢ እና
 • ሎት 4 የተለያዩ ማሽኖችን፣ኮንቴነሮችን፣ብረት እና ሌሎች እቃዎችን የመጫን የማጓጓዝ እና የማውረድ አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም ክሬን፣ ፎርክሊፍት እስካቫተር የደረቅ ጭነት መኪና ክራይ እና 
 • ሎት 5. የመጋዘን ኪራይ የአገልግሎት ግዢ፤

ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ተጫራቾች፡-

 1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የአቅራቢነት ዝርዝር ስዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት ወረቀት (በቅርብ ጊዜ ፕሪንት የተደረገ)፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር ከሚከፈልበት መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ኖክ ማደያ አዲሱ ህንፃ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ/ BID BOND/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርበታል፡፡
 6.  ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃና አገልግሎት ግዢዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
 7. ለሚወዳደሩባቸው እና ናሙና መቅረብ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በተመለከተ ከእየ አይነቱ አንድ አንድ ናሙና የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው የናሙናዎቹን ዝርዝር በሁለት ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት አስቀድሞለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱንብረትሠራተኛአስፈርመው ማስረከብና አንዱን ኮፒ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የተሟላ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት በሰነዱ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሰረት ውሀና መብራት የተሟላለት፣ አስተማማኝ የግቢ አጥር ያለው የጥበቃ ማማ ያለው ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ክፍል እና ለተገቢው አገልግሎት የሚውል የራሱ የጥበቃ ሠራተኞች ያሉት መሆን ይኖርበታል፡፡
 9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተሟላ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት የመጋዘኑን ቦታና ይዘት ለሚመጣው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴ በአካል የማሳየት/ የማስጎብኘት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
 10. በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 11. በተጫራቶች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
 12. አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅፊርማ እና የድርጅቱንመ ማህተም በመምታት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በቅ/ፅ/ቤታችን ስም የጨረታ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለፅ በኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 13. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡15 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
 14. ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን በጽሑፍ ለቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በ5 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች በ15 ቀናት ውስጥ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቀርበው ግዢውን ከሚፈፅመው አካል ጋር ውል ይፈፅማሉ፡፡
 15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-4-70-84-81/011-4-4037-38 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አዲሱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

ግዢና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን