Arbe Gebaya City Administration municipality

Be'kur Hidar 14, 2013

የሊዝ የቦታ ማስታወቂያ

በደ/ጐንደር ዞን በታ/ጋ/ወ/በአ/ገበያ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2013 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የመኖሪያና የድርጅት ቦታዎች በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በደንብ ቁጥር 103/04 አንቀጽ 13/2 በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 17 በሚያዘው መሰረት አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ሁሉ አ/ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ገዝታችሁ መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ፖስታው ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 14/03/2013 ዓ/ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በ10ኛው ቀን 25/03/2013 ዓ/ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት የምትችሉና ሣጥኑ በዚሁ ቀን በ11፡30 ላይ ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት በ11ኛው የስራ ሰዓት በቀን 28/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ዓርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የሚከፈት ሲሆን በ4፡00 ላይ ተጫራቾችም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው ይከፈታል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ካልተስማማበት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሣስባለን፡፡

  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 2680205 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት