Arba Minch University

Addis Zemen Tir 9, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር //12/2013 .

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 2013 በጀት ዓመት ለጠቅላላ አገ/ //ቤት ለሥራ አገ/ የሚውል ጀነሬተር እና Submersible water pump ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

 • ምድብ 1. ጀነሬተር
 • ምድብ 2. Submersable water pump

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት (ዝርዝር) የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ኦርጅናልና የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን/ PPA Online/ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ከሲፒኦ ጋር ኣብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ስለ ጨረታው የሚገልጸውን የጨረታ ሰነድ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ቤት ወይምአዲስአበባበሚገኘው የዩኒቨርስቲው ጉዳይ ማስፈፀሚያ /ቤት ኣራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ቢሮ ቁጥር 14 ዘወትር በሥራ ሰዓት ለፋይናንስና በጀት አስር///ቤት ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቬሎፕ ጥር 24 ቀን 2013 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አገ/ትና ንብረት አስ/ //ቤት ቢሮ በተዘጋጀ ሳጥን መከተት ይቻላል ጨረታው የሚከፈተው 430 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡ ሰነዱ ሽጐ ባይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጐድልበት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ/ምድብ 1 ብር 65,000.00/ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ምድብ 2. ብር 20000.00/ሃያ ሺህ ብር ብቻ
 6. በግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.64 መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው:: የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረታው በተናጠል የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታው ሰነድ በማየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. በከፈታው ቀን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 8. የቴክኒካል ዶክሜንት እና ህጋዊነት ሰነዶችና CPO ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻው ታሽጎ የቴክኒከ ውድድሩን ያለፉት ድርጅቶች ብቻ እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
 9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት ማንኛውንም ወጪ በራሳቸው ችለው ለዩኒቨርስቲው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋሉ፡፡
 10. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታቸውንም ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው::
 11. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስልክ ቁጥር +251111577704 /አዲስ አበባ/

ስልክ ቁጥር 0468811415/0468814533/አርባ ምንጭ/

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ