Arba Minch University

Addis Zemen Tahsas 16, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/16/2013 ዓ.ም

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 በጀት ዓመት ለተማሪዎች መኝታ አገ/ት የሚውል ፍራሽ እና ትራስ፣ ዲያሜንድ ሜሽ ዋየር እና ፍላት ሜታል ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

 • ምድብ 1 – ስፖንጅ ፍራሽ እና ስፖንጅ ትራስ
 • ምድብ 2 – ዲያሜንድ ሜሽ ዋየር እና ፍላት ሜታል

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት (ዝርዝር) የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ vAT/ የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ኦርጅናልና የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው ኣካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቶች በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን PPA Online/ የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሲፒኦ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ስለ ጨረታው የሚገልጸውን የጨረታ ሰነድ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከግዥ አገ/ት ቡድን በአዲሱ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርስቲው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ፅ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት ለፋይናንስና በጀት አስ/ር/ዳ/ፅ/ቤት ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡
 4.  የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቬሎፕ በጥር 3 ቀን 2013 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አገ/ትና ንብረት አስ/ር ዳ/ፅ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀ ሳጥን መክተት ይቻላል ጨረታው የሚከፈተው በ4:30 ላይ ይሆናል፡፡ ሰነዱ ታሽጐ ባይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጐድልበት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል)
 5.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ/ ምድብ 1. 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ ብቻ ምድብ 2. 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ ብቻ
 6. በግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.16.4 መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው:: የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: በጨረታው በተናጠል የሚወዳደሩ አቅራቢዎች ጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታው ሰነድ በማየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. በከፈታውቀን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
 8. . ለምድብ አንድ እና ለምድብ ሁለት ሁሉም ተወዳዳሪ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፣
 9. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ዩኒቨርሲቲው ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት የዋጋ ሰንጠረዥን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፣
 10. ፋይናንሻል የሚከፈተው ናሙናቸው ለተመረጡ ድርጅቶች ብቻ ነው፣
 11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት ማንኛውንም ወጪ በራሳቸው ችለው ለዩኒቨርሲቲው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋሉ፡፡
 12. ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታቸውንም ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።
 13. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 • ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • ስልክ ቁጥር +251111577704 /ኣዲስ ኣበባ/
 • ስልክ ቁጥር 0468811415/0468814533 /አርባ ምንጭ/
 • የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ