Arba Minch Town Municipality

Yedebub Nigat Tir 22, 2013

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት /ቤት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የከተማ ቦታዎችን 17 ጊዜ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በዚህም መሰረት፡

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ደቡብ ንጋት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማዘጋጃ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል እና የቦታዎቹን ዝርዝር መረጃ /Profile/ ከጋዜጣው ላይ፣ ከጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከማዘጋጃ ቤቱ ውስጥ ማስታወቂያ ሠለዳ ላይ በመመልከት መወዳደር ይችላሉ፡፡awashtenders.com /images/downloads/Table3feb.pdf”>http://awashtenders.com /images/downloads/Table3feb.pdf 
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለቦታው የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ፤ የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ እና ቀሪ ክፍያውን የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ /በአመት/ በጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ሙሉ ስማቸውን እና የሚጫረቱበትን የቦታ ኮድ /የቦታ መለያ ቁጥር/ በኤንቨሎፕ ላይ በትክክልና በጥንቃቄ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/ መጠን የጠቅላላ የቦታው ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5 አምስት በመቶ ማነስ የለበትም፣ ይህንንም በፋይናንስ ተቋም በተረጋገጠ የገንዘብ ከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጠናቀቀው ማስታወቂያው በደቡብ ንጋት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 900 ሰዓት ሆኖ የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከቀኑ 1100 ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዘጋጃ ቤቱ ኦሞ አዳራሽ ከጠዋቱ 300 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 5. የንግድ ቦታ ተጫራቾች የማልማት አቅማቸውን ለማረጋገጥ ከጨረታ በፊት በውጭ ኦዲተር ኦዲት የተደረገ የተቋማቸውን የፋይናንስ ሪፖርት ወይም የአንድ ዓመት የባንክ ፋይናንስ ሪፖርት ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. በተጫራቾች በሚቀርበው ሰነድ በሁሉም ገጾች ላይ ሙሉ ስማቸውን ከነአያት፣ ፊርማቸውን፣ የመኖሪያ አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
 7. ጨረታ ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሐሳብ ላይ ለውጥ፣ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 8. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በአኃዝና በፊደል በትክክል የመግለጽ ግደታ አለባቸው፤በአሀዝ/በቁጥር በሚፃፉ ቦታዎች ላይ በአሀዝ ብቻ መፃፍ አለባቸው፡፡ በፊደል በሚፃፉ ቦታዎች ላይ በፍደል ብቻ መፃፍ አለባቸው፡፡ ሆኖም የአኃዙና የፊደሉ ልዩነት ካለው በፊደል የተፃፈው ገዥ/ተቀባይነት ይሆናል/ይኖሯል፡፡
 9. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያውን ሞልተው ካስገቡ በኃላ ሰነድ በመሰረዝ በምትኩ ሌላ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችሉም፡፡
 10. ተጫራቾች ለቦታው የሚያቀርቡት የሊዝ ጨረታ ዋጋ 80%/ፐርሰንት/ የቅድመ ክፍያ መጠን 12%/ፐርሰንት/ እና ቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜ 8%/ ፐርሰንት/ ውጤት ይኖረዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በእነዚህ ሶስት የማወዳደሪያ መስፈርቶች ድምር ውጤት ሲሆን እኩል ነጥብ ያግኙ ተጫራቾች አሸናፊ በሕንፃ ከፍታ የሚለይ ሆኖ በሕንፃ ከፍታም ተመሣሣይ  ከሆኑ በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡ ሴት ተጫራቾች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
 11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድመ ክፍያ መጠን ተጫራቹ ለቦታው የሰጠው የጨረታ ዋጋ በቦታው ስፋት ተባዝቶ ከሚገኘው የቦታው ጠቅላላ የሊዝ ዋጋ ክፍያ፤ ለመኖሪያ 10% /አሥር ፐርሰንት/ ለንግድ ወይም ለድርጅት እና ሌሎች አገልግሎቶች 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ማነስ የለበትም፡፡
 12. የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልፅ ወይም በይፋ ከተገለፀ በኃላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ጨረታው ከተፈፀመ በኃላ ካለው ቀጣይ የሥራ ቀን ጀምሮ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 13. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ሰነድ በላይ በመግዛት በአንድ ቦታ ላይ መጫረት/መወዳደር አይችልም፡፡
 14. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ቦታዎች ጨረታው በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ /ቤቱ ቦታዎቹን ለማስጐብኘት በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በመስክ ለመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
 15. ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሚሰጠው ዋጋ ላይ በመንተራስ ተቀራራቢ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
 16. በጨረታው ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታው ሂደት በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 17. ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ አድራጐት ከፈፀሙ ወይም የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ከሞከሩ

  n