Amhara Water Works Construction Enterprise

Addis Zemen Tir 21, 2013

በግልፅ ጨረታ

የተጫራቾች መመሪያ

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኢው ሲኮድ) ለተመረጡ ቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች GPS Integrated Speed Limiter አቅርቦትና ገጠማ አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ እና ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች ዘግለሰቦች/ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም

መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደር ይችላል።

 1. ድርጅቱየሚፈልገውንለተመረጡቀላልእናከባድተሽከርካሪዎች GPS Integrated Speed Limiter አቅርቦትና ገጠማ አገልግሎት ግዥ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) በስማቸው ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 2. ተጫራቾች የተጠየቁትን ለተመረጠ ቀላልእና ከባድ ተሽከርካሪዎች GPS Integrated Speed Limiter እቅርቦትና ገጠማ እገልግሎት ግዥ የሚያቀርብን ዋጋ መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። በመሆኑም በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ከተገኘ ሰነዱን በሞላው አካል መፈራረም  ይኖርበታል ካልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ብቻ ተለይቶ ከውድድር ወጪ ይደረጋል።
 3. በሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ሕጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ፊርማና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።
 4. ተጫራቾቶ የሚሰጠት ቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች GPS Integrated Speed Limiter  አቅርቦትና ገጠማ አገልግሎት ግዥ እና ሌሎች ከእቃው ጋር የተያያዙ የነወም ወጪዎች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተጠቃለው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
 5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 20 ቀን በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 6. በዚህ ጨረታ የሚሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ሰነዱ ለድርጅታችን ከደረሰበት እና ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት የፀና ይሆናል።
 7. ተጫራቾች እቃውን የሚያቀርቡበት ጊዜ (Delivery Time) ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ 4 (አራት) ወር ጊዜ ይሆናል።
 8. ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ከተመረጠ ያለምንም ቅድመ ክፍያ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር ለ90 ቀን እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ በድርጅታችን ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል የባንክ /Unconditional Bid bond/ በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊ ከተለየ በኋላ እና ውል እንደተያዘ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል።
 10. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በፖስታው ላይ በትከከል በመፃፍና በጥንቃቄ በማሸግ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራከሽን ድርጅት በድርጅቱ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
 11. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም እንኮንድሽናል ባንክ ስድ ጋራንቲ በማሰራት ማስያዝ እና ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት። ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው። የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል።
 12. ድርጅ ፡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታውቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-226 1479በመጠቀም መጠየቅ ያትላሉ፡፡

የአማራ ውሃ ሥራዎች

ኮንስትራክሽን ድርጅት