ሀገር አቀፍ የሊፍት ግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር NCB AWWCE04/2013

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለተለያዩ እየተገነቡ ለሚገኙ ሕንፃዎች አገልግሎት የሚዉሉ ሊፍቶች ኣቅርቦትና ገጠማ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

 1.  የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ ፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት። ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለ120 ቀን እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ሂሳብ ክፍል ገቢ አድርገዉ ኦርጅናል ደረሰኝ በማቅረብ ማስያዝ ወይም በድርጅታችን ስም የተሠራ ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bid bond/ በማሠራት ማስያዝ አለባቸዉ። አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊዉ ጋር ዉል ከተያዘ በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
 3. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ለተገለጹት ሊፍቶች የሚያቀርቡት ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ በተናጠል ከሚያሳይ ብሮሸር ጋር ማቅረብ አለባቸው።
 4. ተጫራቶች እቃዎቹን የሚያቀርቡበት ጊዜ /Delivey time/ ዉል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ 90 ቀናት (ዘጠና ቀናት) ይሆናል። L/C (ሌተር ኦፍ ክሬዲት) እንደመስፈርት ተደርጎ አይወሰድም።
 5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አዉስኮድ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
 6. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ዉሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታዉ በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከዉድድሩ አይታገዱም። ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስነስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛዉም ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የድርጅቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
 7. የጨረታዉ አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ቢድ ጋራንቲ በማሠራት ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የዉል ስምምነት መያዝ አለበት። ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው። የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል።
 8. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ባህርዳር ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የአማራ ዉሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል በድርጅቱ አካውንት ቁጥር 1000265163223 CBE በማስገባት ሙግዛት ይችላሉ። የሚገዙትን የሊፍቱ አቅርቦትና ገጠማው ዓይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ::
 9. ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታዉ ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፣ ለወደፊቱም ድርጅታችን በሚያወጣዉ የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
 10. የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ90 /ዘጠና ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል። ከተጠቀሱት ቀናት በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
 11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 • ይህንንምበሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለጻል።
 • መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት በስልክ ቁጥር፡058 222 14 79 መደወል ይችላል::
 • አድራሻ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ጠቅሳሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት
 • አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አዉስኮድ)
Category:
Installation, Maintenance and Other Engineering Services, Installation, Maintenance and Other Engineering Services, Equipment and Accessories, Equipment and Accessories, Mechanical

Company Name:
Amhara Water Works Construction Enterprise

Company Amharic:
የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

Posted Date:
Hidar 30, 2013

Opening Date:
በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት

Ending Date:
በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት

Newspaper:
Addis Zemen

Newspaper Publish Date:
Addis Zemen Hidar 30, 2013

Publish Date:
Hidar 30, 2013

Company image
<img style="height:50px;width:50px;border-radius:50%;" src="https://tender.awashtenders.com /img/companies/palceholder.png?1556635970″/>

Address
ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

Phones
[‘+251 58 2264778’, ‘058 226 52 03’, ‘058-220-70-51’]

Fax
+251 58 2266011

Bid document price
200 (ሁለት መቶ ብር)

Bid Bond
200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) ብር