Amhara Water Works Construction Enterprise, የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

Addis Zemen

አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 19/2012 

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራከሽን ድርጅት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡ 

 1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20(ሃያ) ተከታታይ ቀናት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ4 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሯችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ወይም በደርጅታችን የባንክ አካውንት ቁጥር 1000265163223 የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የክፍያ ማረጋገጫውን ማስረጃ ይዞ በማቅረብ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በሚገኘው የድርጅቱ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡ ዝርዝር የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ዓይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 
 3. ግዥ ፈጻሚው አካል ከኣሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት ዝርዝር መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 30% (ሠላሳ በመቶ) መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፣ 
 4. ተጫራቶች በድርጅታችን ስም የተሠራ በሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /unconditional Bid bond/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 40,000.00 (አርባ ሽህ ብር) ማስያዝ አለባቸው:: 
 5. ተጫራች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለጹት ዕቃዎች የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተናጠል ማቅረብ አለባቸው። 
 6. ተጫራቶች እቃዎቹን የሚያቀርቡበት ጊዜ /Delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ 45 (እርባ አምስት) ቀን ይሆናል፡፡ 
 7. ተጫራቶች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮፒ ኦርጅናል በማለት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: 
 8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀነ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡ 
 9. አሽናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ 7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ቀርቦ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ ቀርቦ ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡ የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል፡፡ 
 10. አሽናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን እቃ ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረት ክፍል ድረስ ማንኛውንም ወጪ ሸፍኖ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ 
 11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ በድርጅታችን ባለመያዎች ጥራቱ እየተረጋገጠ በድርጅታችን ንብረት ክፍል ገቢ ከሆነ በኋላ ድርጅታችን ሙሉ ክፍያውን የሚፈጸም ይሆናል፡፡ 
 12. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች የጨረታው ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፣ ለወደፊቱም ድርጅታችንበሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡ 
 13. ተጫራቶች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈት በኋላ ለ60 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡ 
 14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለጻል፡፡ 
 15. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን እቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቁ ጊዜ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 • ለበለጠ መረጃ ዘወትር በሥራ ሰዓት በስቴክ ቁጥር፡-058 222 1479/0983568731 መደወል ይችላሉ:: 
 • አድራሻ፡– ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት 

አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት