ANRS Seed Enterprise

Be'kur ሐምሌ27፣2012

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ካለቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ

 • የመኪና ጎማ ለመግዛት ፣
 • ያገለገለ ኮምባይነር ጥራት ንፁህ ጤፍ የተበጠረና ያልተበጠረ፣
 • ለዘር የማይውልና የተለያዩ ሰብሎች ብጣሪ እና የብር ሸለቆ ላይ ያለ ያገለገለ ኮምባይነር ለመሸጥ
 • እንዲሁም የ2012 ዓ/ም በጀት ዓመት በውጭ ኦዲተር የሂሳብ ምርመራ በተፈቀደላቸዉ
 • ኦዲተሮች ኦዲት ማስደረግ እና IFRS መሰረት የተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ፣
 • የ2011 በጀት ዓምት የሂሳብ ሪፖርት IFRS መሰረት እና የ2010 በጀት ንፅፅራዊ የሂሳብ ሪፖርት ማረጋገጥ፣በተፈቀደላቸዉ ኦዲተሮች ስራዉን ለማሰራት በግልፅ ጨረታአወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

 1. ኦዲትን በተመለከተ የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
 2. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ ለመስጠት እውቅና ካላቸው)፣
 3. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
 6.  ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/” ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጫራታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 3 በተገለፀዉ የስራ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::
 7.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፣ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
 8. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ ክብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡ስርዝ ድልዝ ካለዉ አንድ ጊዜ ብቻ አግድም መስመር በማድረግና ፓራፍ ካልተደረገበት ተቀባይነት አይኖዉም፡፡
 9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ባሕር ዳር በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ ዋና መ/ቤት መጋዝን ድረስ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የሽያጭ ሰብሎችን እና እቃዎችን በሚመለከት ግን ከጣቢያው ድረስ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ተጫራቾች የብጣሪ እና ለዘር የማይሆኑ ሰብሎችን ከቦታው ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡
 11. ከሚሸጡት ሰብሎች ጋር በተያያዙ የማስጫኛ የማውረጃና ሌሎች ወጭዎች በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡
 12. ንግድ ፈቃድ የሌለዉ ሰዉ የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
 13.  ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 14. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
 15.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583208415/0983583646 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ