Amhara Construction Works Enterprise

Addis Zemen መስከረም8፣2013

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 05/2013 

የአማራ ህንጻዎች ኮንስትራክሸን ድርጅት በአገራችን ውስጥ ለሚገነቡ የተለያዩ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችንና ማለትም ቶታል እስቲሸን፣ ሊሸሊንግ፣ሬዲዮ መገናኛ እና የብረት ጥራት መፈተሻ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችና ማሳሰቢያዎች ወቅት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል:: 

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ 
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ 
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 4. ተጫራቶች በጨረታለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር፡1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣ 
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ በእያንዳንዱ መሣሪያ በተጠቀሰው የብር መጠን ልክ በብሔራዊ ባንክ እውቅና ከተሠጣቸው ባንኮች ብቻ አሰርተው ማቅረብ አለባቸው። የሚዘጋጀው የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ስድርጅታችን ስም አማራ ህንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (AMHARA BILDING WORKS CONSTRUCTION ENTERPRISE) ተብሎ መሆን አለበት። 
 6. የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ንግድ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጨማሪ ምርጫ CPO/ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላውን ግዥ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል። 
 7. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ/ባህር ዳር አባይ ማዶ ኮበል ፊት ለፊት ባለው እስፓት 300 ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአህስኮድ ዋና ቢሮ ወይምአዲስ አበባ አራት ኪሎ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ ካለው አልማ ህንጻ ከሚገኘው የአህስኮድ የአ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር፡- 0111265652/ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፤ 
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዱን አንድ ላይ በማድረግ “ዋና እና ቅጅ” ለየብቻ በፖስታ አድርገው በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግልፅ የሚታይ የተጫራች ድርጅቱን ማህተም በመወዳደሪያ ሰነዱ ላይና በማሸጊያ ፖስታው ላይ በመምታት በድርጅታችን የማሽተሽ/ግዥና አቅ/ኬዝ ቲም ቢሮ ባህር ዳር የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት ኢማ ግቢ ውስጥ/ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 
 9. ረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የማሽ/ተሽ ግዥና አቅኬዝ ቲም ቢሮ ባ ባህር ዳር የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት ኢማ ግቢ ውስጥ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። 
 10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ 

ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 0583205185/091878390 ወይም 

ፋክስ ቁጥር 0582180538 በመላክ ማግኘት ይችላሉ። 

የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን 

ድርጅት ባህር ዳር