• Amhara

Nebaru Chilga Woreda FEDB

Be'kur ጥቅምት16፣2013

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለነባ/ጭ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች የ2013 በጀት አመት አጠቃላይ ግዥ ማለትም

 • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ
 • ሎት 2 የጽዳት እቃ
 • ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
 • ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ
 • ሎት 5 የጣውላ ቤት ስራዎች
 • ሎት 6 ፈርኒቸር
 • ሎት 7 የደንብ ልብስ ብትን
 • ሎት 8 የደንብ ልብስ ጫማ
 • ሎት 9 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ
 • ሎት 10 የስፖርት ትጥቅ
 • ሎት 11 የመኪና ስፔር ፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. በፍትህ ውል መውሰድ የሚችሉ፣
 5. የግዥው መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 6. የሚገዙ የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
 7. በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በጀርባው ላይ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም፣ ስም፣ ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 30 ብቻ ለረዳት ገ/ያዥ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 10. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ዋናና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በነባሩ ጭልጋ ወረዳ ውስጥ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ፖስታዉን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋት በ4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡
 11. 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 12. ለሁሉም ምድቦች አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለፀላቸው ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል በመውሰድ ነባሩ ጭልጋ ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ዕቃዎቹን በጥራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 13. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 14. አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 15. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይቻላል፡፡
 16. አሸናፊዎች የሁሉም ምድብ ዕቃዎች የሚያቀርቡት ነባሩ ጭ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሣቸው ወጭ ይሆናል ፡፡
 17. ተጫራቾች ለውድድር ከቀረቡ በኋላ ሃሣባቸውን መለወጥ/ማሻሻል/ ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 18. ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን /የሥራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 580 333 0326 ወይም 058 333 1227 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡
 20. የጨረታ አሸናፊውን የምንለየው በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ሁሉንም አይተሞች መሞላት አለባቸው ክፍት መሆን የለበትም፡፡

 • ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች በናሙናው መሰረት መሆን አለባቸው፡፡
 • ናሙናው ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 •  በየገፁ የድርጅትዎ ማህተምና ፊርማ ይደረግበት፡፡

የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት