Benishangul Gumuz Region Sport Commission

Addis Zemen Tir 28, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2013

የቤ/ጉ/ክ// ስፖርት ኮሚሽን 2013 በጀት ዓመት ለታዳጊ ወጣት ፕሮጀክት ማሰልጠኛ ትጥቅ አገልግሎት ለሚውል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ

 • የስፖርት ትጥቅ እና
 • የተለያዩ መጠን CC ያላቸው የሞተር ሳይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

ለዚህም ተጫራቾች ቀጥሎ በተመለከተው መስፈርት መሠረት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡

ሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 1. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት በክልል(በፌዴራል) ደረጃ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ሰርተፍኬት ያላቸውና ከጨረታ ውድድር ያልታገዱ መሆን ይገባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት /አበባ ከኢ... ስፖርት ኮሚሽን ግዥ/ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ የኢትዮጵያ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ ::
 3. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶችና የሚወዳደሩበትን የአንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ ከቫት በፊትና በኋላ ያለውን በትክክል በማስላት በአንድ ኦርጅናል እና በሁለት ኮፒ ለያይተው በየውስጥ ገጾች እና በየፖስታው ጀርባ በድርጅቱ ህጋዊ ሥልጣን በለው አካል ፊርማና ክብ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ድረስ ማስገባት ይችላሉ ::
 4. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙናውን ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ይዘው በመቅረብ ማሳየት አለባቸው በባህርያቸው ክብደት ያላቸውን እቃዎች በየስቶካቸው ማሳየት ይችላሉ።
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት አንስቶ በተከታታይ ቀናት በሚቆጠር በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ 430 ላይ ታሽጎ ወዲያው 500 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣዩ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
 6. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸውን የተጫራቾች መመሪያን ማንበብና መተግበር አለባቸው ::
 7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000(አምስት ሺህ ብር) ህጋዊ ሰውነት ካለው ባንክ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው :: ውድድሩ እንዳበቃ ለተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 8. አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ 10% ማስያዝ ይገባቸዋል :: አሸናፊ ድርጅቶች በመንግስት የግዥ መመሪያ መሠረት የሽያጭ አገልግሎት ዋጋን መከፈል ይገባቸዋል፡፡
 9. አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ 7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ውል መግባትና ውል በገቡ በ15 ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ማስረከብ አለባቸው፡፡
 10. የመንግስት ግዥ አዋጅ እና መመሪያዎች ግዴታቸውን በማይወጡት አሸናፊ ተጫራቾች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡
 11. አሸናፊ ድርጅቶች ባቀረቡትና ተቀባይነት ባገኘው ናሙናና አሸናፊ በሆነባቸው እቃዎች ዓይነት ጥራትና መጠን ጠብቀው ማቅረበ አለባቸው፡፡
 12. የክፍያ ሁኔታ በሚመለከት ቢሮው እቃዎቹን እንደተረከበ በትራንስፈር፧ በቼክ፤ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ለየድርጅቶቹ ክፍያን ይፈጽማል፡፡ በዚህ ጨረታ የቅድመ ክፍያ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም ፡፡ የማስረከቢያው ቦታ አ/አበባ ላይ ይሆናል፡፡
 13. በነጠላና በድምር ዋጋ መካከል ልዩነት ቢፈጠር የነጠላ ዋጋ ገዢ ይሆናል፡፡
 14. ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም::
 15. ጨረታውን የሚፈርመው አካል ወኪሉ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ መያያዝ አለበት ::
 16. የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ ለስድስት ወር ጸንቶ ይቆያል፡፡
 17. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 18. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 0577752431 እና 0911535379/ 0917172042/ 0917183866 መጠቀም ይችላሉ፡፡
 19. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ/// ስፖርት ኮሚሽን