Butajira City Administration

Addis Zemen Tir 25, 2013

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት በእሬሻ ከፍለ ከተማ ለሆስፒታል ግንባታ የሚሆን ቦታ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተሳለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር በማዘጋጃ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከብር 200 / ሁለት መቶ / በመግዛት መወዳዳር ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የስራቀናት ውስጥ ለቦታው የሚያቀርቡትን ዋጋ፣ የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ እና ከፍያ የሚያጠናቀቁበትን ጊዜ በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጠናቀቀው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሃያኛው የሰራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሆኖ የጨረታ ሣጥን የሚታሽገው በዕለቱ ከቀኑ 11፡00 ይሆናል ። ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 2:30 ሰዓት ይከፈታል።
 5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በሁሉም ገጽ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፣ አርማቸውን፣ የመኖሪያ አድራሻቸውንና ስልካቸው ማስፈር አለባቸው።
 6. ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 7. ተጫራቶች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በኣሃዝና በፊደል መግለጽ አለባቸው ሆኖም የአሃዝና የፊደል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ገዢ ይሆናል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸውን ሞልተው ካስገቡ በኋላ ሰነድ በመሰረዝ በምትኩ ሌላ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችሉም::
 9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80% ነጥብ ቀድሞ ክፍያ መጠን 12% ነጥብ እና ቀሪ ከፍያ የማጠናቀቂያ ጊዜ 8% ነጥብ ይኖረዋል፡፡ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነዚህ ሶስቱ ነጥቦች ድምር በሚገኘው ውጤት ይሆናል፡፡
 10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድሚያ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ክፍያ ከዐ% ማነስ የለበትም፡፡
 11. የጨረታው አሽናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጸ በኋላ በጨረታው የተሸነፈ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ /CPO/ ጨረታው ከተፈፀመ በኋላ ካለው የስራ ቀን ጀምሮ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 12. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ የጨረታ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም
 13. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ቦታዎች ጨረታው በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10/አስር ቀናት ጠዋት ከ2፡30 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ቦታዎችን በመዘዋወር መመልከት ይችላሉ፡፡
 14. ሌላ ተጫራች በሚሰጠው ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 15. በጨረታው ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታው ሂደት በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 16. ተጫራቶች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ አድራጐት ከፈፀሙ ወይም የጨረታው ሂደት ለማዛባት ከሞከሩ ከጨረታው የሚታገዱ እና ያስያዙት /CPO/ ለመንግስት ገቢ እደሚደረ ግና በአመቱ በሚካሄዱ ጨረታዎች የማይሣተፉ ይሆናል፡፡
 17. አሸናፊ ተጫራች ስሸናፊ መሆኑ ከማዘጋጃ ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ያስገባውን ቅድመ ክፍያ በመከፈል ውል መግባት ይኖርበታል፡፡
 18. ተጫራቾች ለሚገነቡት ሆስፒታል ፕሮጀክት ፐሮፖዛል እና የአቅም ማሳያ የጠቀላላ የኘሮጀክት ወጪን 30 በመቶ በዝግ አካውንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 19. ተጫራቶች ከስድስት ወር በፊት የነበረ የባንክ ስቴትመንት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያያዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው: በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2013 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ሆስፒታል አገልግሱት የሚሆን ቦታ ስሊዝ ጨረታ የቀረበ ቦታ መገለጫ

ተቁ

ቦታው የሚገኝበት አካባቢ

የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር

የቦታው አድራሻ

ለጨረታ የቀረበ ፕሎት ብዛት

የቦታው ደረጃ

 

የቦታው አገልግሎት

የሚገነባው ህንፃ ከፍታ  

የጨረታ መነሻ ዋጋ  

የሊዝ ጊዜ

የጨረታ ዓይነት  

የክፍያ ማጠናቀቂያ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ

 

ክ/ከተማ

ቀበሌ

11940M2

እሬሻ

01

1

3ኛ

ለሆስፒታል ግንባታ

G+4

348.21

70

ልዩ ጨረታ

40

200.00