Burji Liyu Woreda F/E/D/Bureau

Addis Zemen Tahsas 14, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ////// የቡርጂ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ፅህፈት ቤት 2013 በጀት ዓመት ለሴክተር /ቤቶች አገልግሎት የሚውል

 • የጽ/መሣርያ፣
 • የእንስሳት መድኃኒት፣
 • የደንብ ልብስ፣
 • የደን ዘር እና
 • የሕንጻ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ለበጀት ዓመቱ የፀና ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ተጫራቾች ይጋብዛል።

ስስዚህ፡-

 • 1ኛ. ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ከሚገኙ ተመሣሣይ አካል የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና የምሥክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ አግባብነት ያለው ከሚወዳደርባቸው እቃዎች ጋር የሚዛመድ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተጨማሪ እሴትታክስ (VAT) ማስረጃ፣ ግብር ስለመከፈላቸው የምገልጽ ማሥረጃ (ክሊራንስ) የንግድ ምዝገባ ምሥክር ወረቀት እናበጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 • 2. በጨረታ ሠነድ ላይ የተቀመጡትን መመሪያዎችን የሚያሟሉ  ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበ ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው በተከታታይ ቀናት 1130 ሰዓት ድረስ በቡርጂ ልዩ ወረዳ //ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል በ100 ብር መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • 3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት  ጨረታ ዓይነት 10000 / አሥር ሺህ ብር የመንግሥት እውቅና ካለው ባንክ የተመሠከረለት (CPO) ከመወዳደሪያ ሠነዶቻቸ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • 4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ በግልፅ የመወዳደሪያ ሠነዳቸውን ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋት እስከ 400 ሰዓት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • 5 የጨረታ ሣጥን የጨረታውን ሠነድ በገባበት ዕለት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የበዓል ዕለት ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡
 • 6. የጨረታው አሸናፊ ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመግባት በራሱ ትራንስፖርት እስከ /ቤቱ ድረስ አምጥቶ እቃው 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስገባት ይኖርበታል።
 • 7 ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
 • 8 ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው  የጨረታ ሠነድ (ቅጽ) ብቻ መሙላት አለባቸው።
 • 9 /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 1. የእንስሳት መድሃኒት አቅራቢዎች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርብ እና ጅምላ አከፋፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማሥረጃ ማቅረብ አለባቸው።
 2. የደንብ ልብስ አቅራቢዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ለበለጠ መረጃ:- 0464720093/0927132167/0972629412

 በደ////// የቡርጂ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ፅህፈት ቤት