Bure City Health Post

Be'kur Hidar 7, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የቡሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በ2013 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች

 • ሎት 1 የደንብ ልብስ
 • ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች
 • ሎት 3 የህትመት እና
 • ሎት 4 የፅዳት እቃዎችን በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
 3. ማንኛውም ተጫራች ከ200 ሺህ ብር በላይ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ እና የቫትንም ዋጋ ጨምሮ ሞልቶ መጫረት አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ ጤና አጠ/ጣቢያ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 27 በተ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ ረፋዱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 27 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
 10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫሪቾች ላወጡት ዋጋ ጤና ጣቢያው ተጠያቂ አይሆንም፡፡
 11. ከብር 10 ሺህ በላይ ሽያጭ ከተፈፀመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ 2 በመቶ ይቀነሣል፡፡
 12.  መ/ቤቱ የጨረታ ዋጋውን የሚለየው በየሎቱ በነጠላ ወይም በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
 13.  በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 7740101 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ርክክብን በተመለከተ ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት እቃውን በባለሙያው እያሣዩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

የቡሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ