Sidama Regional State Education Bureau

Addis Zemen Tir 23, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 05/2013

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ለ2013 በጀት ዓመት በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ሊያሰራ ባደው የመማሪያ ህንፃ ብሎክ እና የሽንት ቤት ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት

 1.  ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2013 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ሰሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው እና ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም እግባብነት ካለው መንግስታዊ ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችልህ
 2. በፈዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌብ ሳይት እትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ሚችሉ ወይም በክልሉች በእቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሁበቶችን በግላቸው እቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ፡፡
 4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ እፈጻጸም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
 5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር እለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋና ጋር ተመሳከሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
 6. አንድ ተቋራጭ በእንድ ጊዜ ለአንድ ሎት ብቻ መወዳደር የሚችል ሲሆን ከዚያ በላይ ግን የሌላ ተጨማሪ ሎት ጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
 7. ሎት1 እና ሎት 2 ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገረጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በእንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
 8. ሎት3, ሎት 4 ሎት5 እና ሎት 6 ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000.00 (ሰማኒያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ያኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በእንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
 9.  የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተዕታ MAT/ የተመዘገቡበትን ሰርትፍኬትና ታክስ ክሪላንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 10. የሥራ ተቋራጮች የጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ ይችላሉ
 11. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና እርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል እንድ ዋና ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማስገባትና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም ማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ማስከበሪያው ከቴከኒካል ሰነድ ጋር እብር ማሸግ እለሳቸው።
 12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም።
 13. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
 14. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቀጥር 046-221-00-75 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ