Sululta City Administration FEDB

Addis Zemen Tir 7, 2013

ለሁለተኛ ጊዜ

የወጣ ግልፅ ጨረታ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሱሉልታ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት 2013 የበጀት ዓመት ለሱሉልታ ከተማ ማዘጋጃ /ቤት

 • የተለያዩ ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራጮች ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተል እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ እና TIN ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምሥክር ወረቀት።
 4. ተጫራቹ የሚጫረቱበትን እቃ ናመና (Sample) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች ሠነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው 15ኛው ቀን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሣጥን ይከፈታል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
 7. ተጫራቾች /ቤቱ ካቀረበው መሥፈርት /standard/ በታች መወዳደር አይችሉም፡፡
 8. በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 9. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 10,000 (አሥር ሺህ) በባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ወይም ካሽ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 10.  የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ከታወቀ በኃላ ስተሽናፊዎች ይመለሣል፡፡
 11.  ለጨረታው የሚቀርበው ሠነድ ሥርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።
 12. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 01111860368 መደወል ይችላሉ።

የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና

ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት

ሱሉልታ