North Gonder Zone High Court

Be'kur Tir 17, 2013

የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ቋሪት ቅርንጫ እና በፍ/ባለ እዳ እነ አልማዝ ክቡርና ጓደኞቻቸው ህ/ሽ/ማህበር/10 ሰዎች/ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ የባለእዳው ንብረት የሆነውን በገበዘማርያም ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለእዳ የአቶ ታፈረ ጓሌ መኖሪያ ቤት በምስራቅ መሠረት አረጋ፣ በምዕራብ አስማማው ስንቴ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ሐይማኖት ዘለቀ የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት የግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 854‚000/ስምንት መቶ ሃምሣ አራት ሺህ ብር/ ሆኖ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልፅ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለእዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ የሽያጩ ገንዘብ ውስጥ ቢቻል ሙሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን በምዕ/ጐ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በሞዴል 85 በአደራ የሚያስይዝ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የምዕ/ጐ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት