• Gojjam
 • Applications have closed

Burie Localities FEDB

Be'kur ጥቅምት16፣2013

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የምዕራብ ጐጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ

 • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች
 • ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች
 • ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን
 • ሎት 4 የተዘጋጁ የደንብ ልብስና ብትን ጨርቅ
 • ሎት 5 የሞተር ብስክሌት ጐማና መለዋወጫ እቃዎች
 • ሎት 6 አመታዊ የሞተር ብስክሌት ጥገና የእጅ ዋጋ
 • ሎት 7 አመታዊ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ
 • ሎት 8 የተዘጋጁ/ የተሰሩ/ ፈርኒቸሮች እና የሚሰሩ ፈርኒቸሮች
 • ሎት 9 የስፖርት ትጥቅ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
 3. ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋብር 200 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾ የእቃውን ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በመሂ/1 ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈል የከፈሉበትን ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 01/03/2013 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ መግዛት ሲመጡ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን የውክልና ደብዳቤ/ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶች በየሎቱ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት ምድብ/ውስጥ/ የሚገኙት እቃዎች የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልፃፉ ግን የተሞላውን ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጐ ይወሰዳል፡፡
 11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በየምድቡ/በየሎቱ/ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል/ከቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ ፡፡
 12. ተጫራቾች መ/ቤቱ ካቀረበው ስፔስፊኬሽን ውጭ የራሱን ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙያ ላይ ያስቀመጠ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 13. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ 20 በመቶ ቀንሶም ቢሆን ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
 14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 15.  ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ከሁሉም የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም ሆኖም ግን ስርዝ ካለው ፊት ለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለማየት እና ለመነበብ አዳጋች ከሆነ ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
 16. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች የማጓጓዣ ትራንስፖርት ሙሉ ውጭ ችሎ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ድረስ አምጥቶ በየፑል ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 17.  በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብ/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0237 መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡
 18. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ዓ/ም መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
 19. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡

የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት