• Arsi

West Arsi Zone F/E/D/B

Addis Zemen Tir 28, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የምዕራብ አርሲ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር /ቤቶች 2 ዙር 2013 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም

 • ኤሌክትሮኒክስ
 • ፈርኒቸር
 • የፅህፈት መሳሪያዎች
 • የፅዳት እቃዎች
 • የተለያዩ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች

ከላይ የተዘረዘረውን እቃ በግልፅ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መስፈርት በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዛችዋል።

 1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ክፋይ የሆኑ TIN Number ማቅረብ የሚችሉና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት
 2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቡን በመቀየር የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጓል ቢሞክር ከጨረታዉ ዉጭ በማድረግ በህግ የምንጠይቅ ይሆናል።
 3. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የግዥ መደብ ብር 10,000.00 / አስር ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት /CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን በካሽ ከሆነ በም/////ልጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000018917107 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት::
 4. አሸናፊ ድርጅት እቃዉን ጭነዉ እስከ /ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት::
 5. ተጫራቾች እቃው የተሰራበትን/የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት . ግለፅ አለባቸው::
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በስርአት የታሸገና ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውንና ፋክስ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረምና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው።
 7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም::
 8. /ቤታችን የሚያጫርታቸውን እቃዎች እስከ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል::
 9. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ወይም ለሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል ::
 10. /ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ እቃዉ አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራቱን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዛት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል ::
 11. ሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 28/5/2013 እስከ 18/6/2013 . በ11:30 ሰዓት ሲሆን፣ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን 19/6/2013 . ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በምዕራብ አርሲ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት /ቤት ሻሸመኔ ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል::
 12. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከምዕራብ አርሲ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/በም////////ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000018917107 የኢትዮጵያ ንግድ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 10 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ደርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰአት የሰነዱ ሸያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል።
 13. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውሉ መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት::
 14. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት የጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ////////ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000018917107 በኢትዮጵያ ንግድ ገቢ በማድረግ ውል መግባት ይችላል፡፡
 15. አንዳንድ ጥራታቸውን ለመለየት የሚያስቸግሩ እቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ቀለሞች ቦርሳዎች እና የመሳሰሉ
 16.  /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 046 11100723 ሞባይል 0912265351,