• Gojjam

East Gojam Zone Correctional Center

Be'kur Yekatit 1, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ከመጋቢት 1/2013 እስከ Yekatit 30/ 2014 ዓ.ም ድረስ በስሩ ለሚገኙ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ

 • ሎት 1. የምግብ እህሎችን ፣
 • ሎት 2. ፊኖ ዱቄት ፣
 • ሎት 3. ቅመማ ቅመም እና ጐመንዘር ፣
 • ሎት 4. አትክልት ፣
 • ሎት 5. የተለቀመ በርበሬ ፣
 • ሎት 6.የማገዶ እንጨት በሎት አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህመግዛት የምንፈልገው የእህል አይነትና ብዛት እንዲሁም የሌሎችም አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የሚገኝ ሲሆን መወዳደር የሚፈልግ ህጋዊ ተወዳዳሪ ማሟላት ያለበት፡-
 1.  በዘርፋ ህጋዊ ፈቀድ ያላቸውና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. . ቫት ከማይጠየቅባቸው የምግብ እህሎች ውጭ ባሉት ግዥዎች ከ200 ሺህ ብር በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
 3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ከገንዘብ ያዥ ላይ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሣ ብር/ በመክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በስራ ፈቃዳቸው መሰረት ማቅረብ የሚገባቸውን አቅርቦቶች ለይተው በመሙላት የጨረታ ሠነዱን ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ከመታሸጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቧቸው የእህል እና የማገዶ እንጨት ጠቅላላ ዋጋ ገንዘብ መጠን የጨረታ ማሰከበሪያ የአንድ ዓመት በማስላት 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ፣በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የሚያሲዙ ሲሆን አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማሰከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ በመጨመር 10 በመቶ የሚያሲዝ ሆኖ የተሸነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው በመመሪያው መሠረት የሚመለስ ይሆናል፡፡
 6. ከ10‚000 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ ከሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያው መሰረት 2 በመቶ የሽያጭ ታክስ መክፈል ይኖርበታል፡፡
 7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ወቅት ዋጋ የሞሉበት ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳርፍ አለባቸው፡፡
 9. የጨረታ አሽናፊዎች ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፋባቸውን እቃዎች ማረሚያ ቤቱ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 10. ተጫራቾች ለማቅረብ የተጫረቱባቸውን የምግብ እህሎች ከማገዶ እንጨትና ፊኖ ዱቄት በስተቀር ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 11. የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 11፡00 ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
 12. የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
 13. መምሪያው ጨረታውን አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 771 1636 ደውለው ወይም በአካል ምስ/ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምስ/ጎጃም ዞን ማ ረሚያ ቤቶች መምሪያ