Mehal Meda City Administration FEDB

Addis Zemen Tahsas 27, 2013

 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው ዓይነት መደበኛ ጨረታ ቁጥር 5/2013

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ////ቤት በግ///አስ/ሥራ ሂደት ለመ/ሜዳ ከተማ አስ/////አገ//ቤት 2013 በጀት ዓመት የሚያስገነባው ለመሠረተ ልማት አገልግሎት የሚውል ገረጋንቲ ጠጠር ሴሌክትድ / አቅርቦት፣ የሮሎና ግሬደር ማሽን አቅርቦት ኪራይ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ገረጋንቲ ጠጠር ሴሌክትድ አዣራ አቅርቦት፣ ማሽን አቅርቦት ኪራይ መኮናተር ይፈልጋል፡፡

 1. ገረጋንቲ ጠጠር ሴሌክትድ አሻራ/ አቅርቦት
 2. የሮሎና ግሬደር ማሽን አቅርቦት ኪራይ

ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ ታደሠ የሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
 2. የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው፤
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፣
 4.  የግዥ መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማሥረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
 6. የሚገዙ ገረጋንቲ ጠጠር /ሴሌክትድ አዣራ አቅርቦት፣ የሮሎና ግሬደር ማሽን አቅርቦት ኪራይ በወጣው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሠረት ከጨረታ ሠነዱ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፤
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን መግዥያ የማይመለስ እያንዳንዱ ሠነድ ገረጋንቲ ጠጠር ሴሌክትድ አዣራ አቅርቦት እና የሮሎና ግሬደር ማሽን አቅርቦት ኪራይ እያንዳንዱ 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመፈል ከግ///አስ/የሥራ ሂደት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ገረጋንቲ ጠጠር /ሴሌክትድ አዣራ አቅርቦት 7000 /ሰባት ሺህ/ ብር ብቻ እና የሮሎና ግሬደር ማሽን አቅርቦት ኪራይ 4000 /አራት ሺህ/ ብር ብቻ cpo በመሂ 1 ወይም ከሕጋዊ ባንክ ማስያዝ አለባቸው። ልዩ ልዩ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገ////ቤት በግ///አስ/የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 የተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ከቀኑ 745 ድረስ ሠነዱን በመግዛት ዋጋ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግ///አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ 16 ቀን ላይ ከቀኑ 745 ታሽጎ በዚሁ ቀን 800 ላይ ይከፈታል። የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ ተመሣሣይ ቀን ይከፈታል፡፡
 11.  ከላይ የተጠቀሰው ጨረታ አሸናፊው የሚለየው እያንዳንዱ ሠነድ በድምር ይሆናል፡፡
 12. ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው ማህበራት የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣትና ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በመመሪያው መሠረት ልዩ ድጋፍ ይደረጋል። ኢንተርፕራይዙበሚያመርተው ምርት ላይ ብቻ ሆኖ ሲገኝ፡፡
 13. የጨረታ ጊዜ /ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሐሳብ ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም፡፡
 14. የተጫራቾች መመሪያ፣ የጨረታ ማስታወቂያ እና የውል ቃል ከጨረታ ሠነዱ ጋር አብሮ መመለስ አለበት። ካልተመለሰ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
 15. የቀረበው የዋጋ መወዳደሪያ ጨረታው ከተከፈተበት እለት አንስቶ 30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
 16. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 17. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116851529/28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ////ቤት //