• Amhara

Mekane Eyesus Elementary Hospital

Be'kur Tir 24, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በእስቴ ወረዳ የመካነ ኢየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀትና ከውስጥ ገቢ ከሚገኝ ገንዘብ ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ

 • የደንብ ልብስ ጫማ የቆዳ ውጤቴች  ምድብ 1.1
 • የደንብ ልብስ ጫማ የፕላስቲክ ውጤቶች  ምድብ 1.2
 • የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ  ምድብ 1.3
 • የደንብ ልብስ ተሰፍተው የተዘጋጁ  ምድብ 1.4
 • አላቂ የቢሮ እቃዎች  ምድብ 2
 • አላቂ የፅዳት እቃዎች  ምድብ 3
 • አላቂ የህትመት ስራዎች  ምድብ 4
 • የፈርኒቸር እቃዎች  ምድብ 5
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች  ምድብ 6
 • የውሃ መስመር እና ኤሌክትሮኒክስ መገጣጠሚያ እቃዎች ምድብ 7
 • ቋሚ መሣይ የቢሮ እቃዎች ምድብ 8 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
 3. የግዥ መጠኑ በእያንዳንዱ ምድብ 200 ሺህ ብር እና ከዚህ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መ ረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማስረጃቸውን የዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 02/14 ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ወይም ማግኘት ይቻላል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ስራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኮፒ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአማረኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሣይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋውን በመሙላትና በየገፁ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጐ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 21 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ከጠዋቱ በ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11፡30 በቦታው በመገኘት ፖስታውን ማስገባት ይቻላል፡፡ ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሉ በዚሁ ቀን ማታ በ11፡40 ታሽጐ በነጋታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
 9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሆስፒታሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
 10. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. በጨረታው የሚሣተፍ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0918456133 ወይም 0918173015 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 12. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የስራ ዘርፍ ሁሉንም አይተሞች ወይም ዝርዝሮች መሙላት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጥቅል ድምር ዋጋ ይታያል፡፡
 13.  የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ያሸነፉቸውን እቃዎች በስፔስፊኬሽናቸው መሰረት እና በሞላው ዋጋ መሰረት ከሆስፒታሉ ድረስ በራሱ ወጭ ማምጣት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ በተባለው ስፔስፊኬሽን መሰረት እና በሞላው ዋጋ መሰረት ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ የግዥ መመሪያው በሚያዘው መሰረት ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡
 14. ሆስፒታሉ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን ለመጨመር ቢፈልግ የዋጋ ልዩነት እና የእቃ ልዩነት ሣይኖር ከጠቅላላ የግዥ ዋጋው 20 በመቶ መጨመር የሚችል ሲሆን የማይፈልጋቸው እቃዋች/የበጀት ችግር ቢያጋጥመው/ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋው 20 በመቶ መቀነስ ይችላል፡፡
 15. የጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ከ5 የስራ ቀን በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በምድቡ የሚገዛውን የግዥ መጠን የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ በፍትህ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
 16. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡
 17. የእቃ ርክክብ ቦታ መ/ኢ/የመ/ደ/ሆስፒታል ድረስ በራሱ ወጭ በማምጣት የሚያስረክብ ሲሆኝ የእቃዎቹን ጥራት መጠን በተመለከተ ሁሉም እቃዎች ኦርጅናል መሆን አለባቸው፡፡

የመካነ ኢየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል