• Addis Ababa
  • Applications have closed

Federal Courts Judgement Execution Directorate

Addis Zemen ጥቅምት25፣2013

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወት ዘመዴ ዳኘው እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አለም አከለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 64481 በ14/05/2011 ዓ.ም እና በመ/ቁ 81621 በ11/06/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የቤ.ቁ 1334 የካርታ ቁጥር 06086 አጠቃላይ ይዞታው በአቶ ዳኜ አምባው ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የሚሸጠው ግማሹ የአባት የውርስ ሃብት ብቻ ነው ይዞታው ስፋት በካርታ 400 ካሜ የሚሸጠው 200 ካሜ ነው የሚሸጠው በክፍፍሉ ዋና ቤት ያለው በእስኬች የተመለከተ ሲሆን የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 49,760 (አራት መቶ ዘጠና አንድ ሺ ሰባት መቶ ስልሳ ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቶች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለሙግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት

በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቶች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት