• Gojjam

Liben Primary Hospital

Be'kur Tahsas 26, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕ/ጎጃም/ዞን/የሰ/አቸ/ወረዳ የሊበን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውል

 • ሎት 1 የፅዳት እቃ
 • ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች
 • ሎት 3 የደንብ ልብስ
 • ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች፤
 • ሎት 5 ፈርኒቸር፤
 • ሎት 6 ህትመት ፤
 • ሎት 7 የመኪና አገልግሎት የሚዉሉ ተለዋጭ እቃዎች እና
 • ሎት 8 የኤሌክትሪክ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤

 1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣
 2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር/ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
 3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200 ሽህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደርበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 ከሰ/አቸ/ወ/የሊ/መ/ደ/ሆስፒታል ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈል እና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ተሽጦ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲመጡ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን /ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶችን በየሎቱ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ በዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሰ/አቸ/ወ/የሊ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 09 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. አሸናፊ ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት /ምድብ/ውስጥ የሚገኙትን እቃዎች የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ ፡፡እንዲሁም የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፤ ካልፃፉ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየምድቡ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል የሊ/መ/ደ/ሆ ስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
 12. መ/ቤቱ እነደአስፈላጊነቱ 20 በመቶ ቀንሶም ይሁን ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
 13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረተውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 14. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ከሁሉም የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም ፤ሆኖም ግን ስርዝ ካለው ፊት ለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
 15. አሸናፊ ተጫራች የአሸነፋቸውን እቃዎች ሙሉ ወጭ ችሎ ከሰ/አቸ/ወ/የሊ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ድረስ አምጥቶ ማድረስና ማስረከብ ይኖርበታል ፡፡
 16.  በጨረተው ለመሳተፍ ለሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሺን) በሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 17.  የጨረታ አሸናፊዉ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
 18. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
 19. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 09 38 09 44 63 ወይም 09 18 45 21 20 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሊበን የመ/ደ/ሆስፒታል