• Sidama

Hawassa University

Addis Zemen ግንቦት26፣2012

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝን አወቃቀርና የአሠራር ሥርዓት በተሻስ ሁኔታ በአማካሪ ድርጅቶች ማስጠናት ያመጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ የነበረውን አወቃቀርና የአሠራር ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ በአማካሪ ድርጅት ለማስጠናት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አማካሪ ድርጅቶች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡ 

  1.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN-No) ያላቸው፡፡ 
  2. በአማካሪ ድርጅትነት ለመሥራት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ስለመሆናቸውና በሚመለከተው መንግሥታዊ ፈቃድ ሰጪ አካል ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 30 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ፣ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ላይ ከሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  5. የጨረታውን ማስከበሪያ ለሥራው ማከናወኛ በተወዳዳሪነት ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የሆነውን በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ30ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
  8. የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለጽ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም፡፡ 
  9. የጨረታ ውድድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ የግዥ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ ኣማካይነት ይገለጽላቸዋል፡፡ 
  10. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና ጽ/ቤት፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በፖሊሲ ልማትና ጥናት ተቋም ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ፡፡ 

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0916-86-05-65 / 0930-10-84-15 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ