• Sidama

የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒዩተር፣ፕሪንተር፣ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ሌሎች ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

ጨረታ ማስታወቂያ 

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 

የግዥ መለያ ቁጥር ግፋ/09/2012 

የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች በተገለፀው ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ ፡፡ በዚሁ መሠረት የሚፈለጉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡ 

.

መግለጫ

1

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ኮምፒዩተር፣ፕሪንተር፣ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ሌሎች ዕቃዎች ጨምሮ

  • በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው 

  • የ2012 ዓ/ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ 
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ( የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ 

2. የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ግዥውን  በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከተጠየቀው ሲፒኦ ማስያዣ ውጪ ያቀረበ ጨረታው ውድቅ ይደረጋል፣ 

3. የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግ/ንብ/አስ/ከ/ቲ/አስተባባሪ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣ 

4. ተጫራቾች የጨረታ ዶከመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት ሠነድ ካልያዙ የጨረታ ዶክመንቱ አይሸጥም፣ 

5 የዕቃዎችን ብዛት ተዘጋጅቶ ስሚሸጠው የጨረታ ዶከመንት ላይ በዝርዝር ተገልጿል፣ 

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው፣ 

7.ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት ግ/ንብ/አስ/ኬ/ቲ/አስተባባሪ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡ 

8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል ፡፡ ሆኖም ግን 21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ 

9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  • ስልክ ቁጥር፡- 046 212 1580/ 046 22128826 
  • ፖ.ሣ.ቁ 108 አድራሻ ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር አስፋልት ፊት ለፊት 

የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት