Zewditu Memorial Hospital

Addis Zemen ነሐሴ22፣2012

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 1/2013

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል 2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ከሎት 1 እስከ ሎት -9 የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው።

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚልፅ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
 2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት ቅዳሜ፣ዕሁድና የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10 ኛው ቀን 1000 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ የግዢ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
 3.  ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማህተም ተደርጎ በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒውን በመለየት የሚቀርብ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 4፡10 ድረስ ግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 4. ተጫራቾች ሰነድ ሲያቀርሱ ፋይናንሱን የያዘ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒው ለብቻ ተለይቶ በፖስታ መታሸግ አለበት። ቴክኒካል መስፈርቱን /የንግድ ፈቃድ ፣ቫት ተመዝጋቢነት፣የግብር ከፋይነት ማስረጃ እና ለዕቃው /ለአገልግሎቱ/ ሌሎች ቴክኒካል መስፈርቶችን ለብቻ ኦሪጅናልና ኮፒው ተለይቶ በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
 5. 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 410 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 420 ላይ ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል።
 6.  
 7. 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ፡-

1 በሎት -1 የላውንደሪ ማሽን   ግዥ

 • በሎት-2 የላውንደሪ ክፍል የአጠባ
 • በሎት-3 የተለያዩ መድሀኒት ና ሪኤጀንት ግዥ፣
 • በሎት -5 የዳቦ ግዢ አገልግሎት አውት ሶርስ ግዢ
 • በሎት -9 የህከምና ዕቃ መሳሪያዎች ግዥ ላይ

የብር 10,000.00 (አስር ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) በሆስፒታሉ ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. በሎት-4 የላውንደሪ ማሽኖች አጠባ

 • በሎት -7 የሴክዩሪቲ ካሜራግዢ የጥገና አገልግሎት ግዢ
 • በሎት – 6 የጥልቅ ውሀ ጉድጓድ ፓምፕ ግዢ
 • በሎት – 8 የኤክስቴንሽን የስልክ የመስመር ዝርጋታ ሥራ ግዢ

ብር 5,000.00 (አምስት ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) በሆስፒታሉ ስም የተዘጋጀ ማቅርብ አለባቸው።

 • 7. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
 • 8. ተጫራቾች በሎት-5 የዳቦ ግዢ ላይ የሚወዳደሩ የዳቦ አምራች ድርጅት መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው አሸናፊው ድርጅት የዳቦ አቅርቦቱን የጥራት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል። የሆስፒታሉ ቴክኒክ ኮሚቴ በየቀኑ ዳቦ ሲገባ አይቶና ተቆጣጥሮ ይረከባል። ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ተመላሽ ያደርጋል። ይሄም በውሉ ላይ ይካተታል።
 • 9. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠየቀው መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
 • 10. ተጫራቾች ሳምፕል በሚያቀርቡባቸው ላይ እና ከሆስፒታሉ ስፔስፊኬሽን በቀረበባቸው ላይ ቴክኒካል ግምገማ ስለሚደረግ ተጫራቾች ይሄን በትክክል አይተውና ተገንዝበው ሳምፕል በማቅረብ እና ቴክኒካል መስፈርቱን በማየት መጫረት ይኖርባቸዋል።
 • 11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዥ ዳይሬክቶሬት በጽሑፍ ወይም በቃል ማቅረብ ይችላሉ።
 • 12. የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል።
 • 13 ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 7 ቀን በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ በሰባት ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 • 14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውምሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል።
 • 15 የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል።

ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-515-02-42 በመደወል መረዳት ይቻላል።

አድራሻ፡በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ /ከተማ ፍል ውሀ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል