ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

 

የተበዳሪው

 ስም

የአስያዡ ስም

የንብረቱ አድራሻ

የቦታው ስፋት

የካርታ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

ሐራጅ የሚከናወንበት

ክልልና ዞን

ወረዳ

ቀበሌ

ቀን

ስዓት

 

ምዝገባ

 

መጫረቻ

ቨርዴ ቢፍ ፕሮሰሲንግ  ኃ/የተ/የግ/ማ

ተበዳሪው

ኦሮሚያ ክልል፣ምስ/ ሸዋ ዞን(ዝዋይ/ባቱ ከተማ)

አዳሚቱሉ ጂዱ ኮምቦልቻ

በወይሶ ቀንጫራ

1,300 (አንድ ሺህ ሶስት መቶ)

ሄክታር

BLBENO/BL/1616/1707/08

የከብት ማድለቢያ እና በላዩ ላይ ያሉ ንብረቶች( ዝርዝሩን ከባንኩ ዘንድ ይገኛል)

150,013,604.71

(አንድ መቶ ሀምሳ ሚሊዮን አስራ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አራት ብር ከ71ሣ)

የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

ጠዋት ከ4፡00-5፡30

ጠዋት ከ5፡30-6፡15

 

መን ባንክ አ.ማ. ቨርዴ ቢፍ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ለተባለ ድርጅት ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ግዙፍ የከብት ማድለቢያ (ranch) እና  በላዩ ላይ ያሉ ንብረቶችን( የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ማሽኖች ጨምሮ) ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት  ከስር በተ.ቁ 6 በተጠቀሰው ቦታ  ላይ በሚካሄድ ሐራጅ  አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሐራጅ ደንቦች

1. ተጫራቾች የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት በሀገር ውስጥ ባንኮች የተሰጠ የባንክ የዋስትና ሰነድ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የመታወቂያ ኮፒ እና የውክልና ኮፒ(ሌላ ሰው ወይም ድርጅት የሚወክሉ ከሆነ) ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

3. አሸናፊዎች ባሸነፉበት ዋጋ ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የመክፈለ ግዴታ አለባቸው፡፡

4. አሸናፊ የሆነው/ችው ተጫራች አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ  ያሸነፈበትን/ችበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ/ች ያስያዘው/ችው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል እና ተገቢነት ያላቸውን ህጎች ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡

5. ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡የጨረታ አሸናፊው ስም ከማዞርጋር ያለ ክፍያ፣የሊዝ ክፍያ፤ግብር(ካለ) ይሸፍናል፡፡

6. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ካዛንችስ በሚገኘው በባንኩ ዋና መ/ቤት ስምንተኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡

7. ተጫራቾች ንብረቱን   ከጨረታው ቀን በፊት በስራ ሰዓት ከባንኩ የሕግ ክፍል መምሪያ ተወካይ ጋር በመሆን ፕሮግራም በመያዝ መጐብኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጨማሪ ደንቦችን እና የንበረቱ መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ የተዘጋጀ  በመሆኑ ይህን ሰነድ ከባንኩ የህግ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ይህ ሰነድ የዚህ ማስታወቂያ አካል ነው፡፡

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911152490 ወይም 0919602648 ወይም 0116686215/16.ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

10. ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Joseph Tito St.  P.O.Box 1212     Addis Ababa, Ethiopia

 

Local-Knowledge – International Standards