Wendo Trade and Investment Company

Addis Zemen ነሐሴ3፣2012

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ 

ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድጋሚ የወጣ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ኩባንያው ከሙገር፣ ከደርባ እና ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ኩባንያው አስራ ስምንት የስርጭትና የሽያጭ ጣቢያዎች/ማዕከላት ሲሚንቶ ለማጓጓዝ ህጋዊ የጭነት ትራንስፖርት /የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራትን ድርጅቶችን አወዳድሮ ሲሚንቶ የማጓጓዝ አገልግሎት ሥራ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያባቸው መስፈርቶች፡

 1. ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ የታደሰ የንግድ የምዝገባ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመካፈል የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት እና ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የምዝገባ ሰርተፍኬት እና የተመዘገቡ አባላት ዝርዝር ውስጥ መኖሩን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ 
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ እና የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ ኮፒ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ድርጅታችን በሚገኝበት መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ ፋይናንስ ግዢ/ን/አስ/መምሪያ በመምጣት ማስታወቂያው በድጋሚ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከወንዶንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መ/ቤት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ፋይ/ ግ/ን/አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 4. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 5. የጨረታ ማስታወቂያው በድጋሚ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው(አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡ 
 6. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም በትራንስፖርት/የጭነት አገልግሎት ሥራ ለዲስት ምስክርነት የሚሠጡማስረጃዎችን እንደዚሁም ስርዝ ድልዝ የሌለው የመጨረሻ የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኩባንያው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 7. የጨረታ አሸናፊ እንደተገለፀለት በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10/100 (አስር መቶኛ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ የስምምነቱን ውል ይፈርማል፡፡ 
 8. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈራረመ በኋላ ትክክለኛውን ተረክቦ የጫነውን ሲሚንቶ ወደ ድርጅቱ የስርጭትና የሽያጭ ጣቢያዎች ንብረት ክፍል ስማድረስና ገቢ በማድረግ በውሉ መሠረት የጭነት አገልግሎት ክፍያውን በደብዳቤ ሲጠይቅ የጥያቄው ትክክለኛነት በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ተረጋግጦ ክፍያው ይፈፀማል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ 
 10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ 
 11. የጨረታው ሣጥን በሚከፈትበት ወቅት ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ወይም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
 12. መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ ወይም ግልጽ ያልሆነ ጉዳይ ካለ በስልክ ቁጥር መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ 

ስልክ ቁጥር 011 552 10 09/011 552 14 58 

-ፖሣቁ9515 

-ፋክስ 011 551 3654 

የወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር