• Amhara

Kombolcha Correctional House

Be'kur Tir 17, 2013

በድጋሜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ማረ/ቤቶች ኮሚሽን በደ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ ለኮምቦልቻ ማረሚያ ቤት ለ2013 ዓ.ም የበጀት አመት አገልገሎት የሚውል

 1. ደንብ ልብስ
 2. ህትመት
 3.  የህክምና እቃ
 4. ለታራሚዎች የምግብ እህል እና ሸቀጣሸቀጥ
 5. የመኪና መለዋወጫ እቃ
 6. የጥገና እቃ /ህንፃ መሳሪያ/
 7. ማሽነሪ እቃዎች
 8. ቋሚ እቃዎች እና ሌሎች የቤት ውስጥ ተገጣጣሚ እቃዎች
 9. የጭነት እና የሙያ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በየዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
 3. የግዥ መጠኑ በሎት ብር 50.000 /አምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ስርአት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚቻል ሲሆን ጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለገንዘብ ያዥ ሲፕኦ ከሆነ ለገንዘብ ያዥ ወይም ከሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
 5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያዘበት የጨረታ ሰነድ መወዳደር አይችልም
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የድርጅቱን ስም ፤አድራሻ ፤ ማህተም፤ ፊርማ በማድርግ በሚነበብ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. የጨረታ ሰነዱና መረጃው የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 8. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል በኮምቦልቻ ማረ/ቤት ግዥና ፋይናስ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል፡፡
 9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙናውን ለማረ/ቤቱ በማቅረብ ማሳየትና ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 10. ተጫራቾች በጨረታ ሰ ነዱ ላይ ቫቱን ጨም ረው መሙላት ይጠበቅባቸዋል ፡፡ የጨረታ ፖስታው ከተከፈተ በኋላ ቫት ያስጨም ራል ቢሉ የጨረታ ሰ ነዱ ተቀባይነት የለዉም፡፡
 11. አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ወይም በጥቅል የዋጋ ድምር /በሎት / መ/ቤቱ በመረጠው መንገድ ይሆናል፡፡
 12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን በየሎታቸው በተለያየ ፖስታ በማሸግ በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋውን እቃ ሙሉ ወጭውን በመቻል በኮምቦልቻ ማረሚያ ቤት ግቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 14. አሸናፊው ድርጅት በተጠየቀው ዝርዝር መሰረት ጥራቱን የጠበቀ እቃ ካላስረከበ በገዛ ኪሳራው እቃውን የመቀየር ወይም የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
 15. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ግ/ፋ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ከቀኑ 11፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስአት ይከፈታል፡፡
 16. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
 17. የጨረታ አሸናፊው ያልተገጣጠሙ ወንበር፤ ጠረንጴዛ፤ እና ማሽነሪዎችን ገጣጥሞ በማረ/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
 18.  የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸለት በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቀርቦ ውለታ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
 19. የታራሚዎችን የምግብ አቅርቦት አሸናፊው ፍትህ ፅ/ቤት በመቅረብ ለአንድ አመት ያክል ለማቅረብ ውለታ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡
 20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 21. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-551-06-76 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ዋጋውን ሲ ሞሉ ቫቱን ጨምረው ይሙሉ

የኮምቦልቻ ማረሚያ ቤት