ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተለወጡ የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

      ተሽከርካሪዎችንና የተሽከርካሪ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ ቃሊቲ ቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በካፍደም ሲኒማ ወደ ዉስጥ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካን አለፍ ብሎ በሚገኘው የኩባንያዉ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ በቆሙበት የካቲት 30 ቀን 2012 ጀምሮ  በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ፡፡

      በተጨማሪ 3 ቦቴ ታንከር መቀሌ የሚገኝ ፤አንድ 40ፊት ኮንቴነር አፋር የሚገኝ እና አንድ 20ፊት ኮንቴነር ኮምቦልቻ የሚገኙ ስለሆነ ባሉበት መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡

      ጨረታው መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከጧቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

      ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ የመነሻ ዋጋዉን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የጨረታ ማሰከበሪያው ለተሽከርካሪዎች ከብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) እንዲሁም የተሽከርካሪ አካላት ላይ ከብር 500.00(አምስት መቶ) ማነስ የለበትም፡፡

      ሌሎች ተጫራቶች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡ 

      በተሽከርካሪዎችና ሌሎች አካላት ላይ ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡

      የጨረታዉ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ፡፡

      አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን መረከብ ዕቃዎቹንም ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለባቸዉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡

      ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 111 97 71/70 ወይም 011 126 39 94 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰዉ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡

      ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ