የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 0BU-ONT-02-2013

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ (Incubator) እና ተዛማጅ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል።

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፦

1.የጨረታ ሰነዱን ከታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ Tahsas 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታ ሣጥን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ 4 ኪሎ ሮሚና ካፌ አጠገብ በሚገኘው ጀርመን ህንጻ ሐረማያ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ቁጥር 15 ይከፈታል።

  • 3.1 በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ።
  • 3.2 ማንኛውንም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመከፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፡፡
  • 3.3 በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስከር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፡፡
  • 3.4 ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ ኖርባቸዋል፡፡
  • 35 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4 ተጫራቾች ግዥ ማስረከቢያ ቦታ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

5. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

7. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የጫኝና አውራጅ አካተው ማቅረብ አለባቸው።

8. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

ስልከ ቁጥር 0255510878/1606/ 1610

ፋክስ ቁጥር 0255510182 

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ጭሮ

አዲስ አበባ አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ አጠገብ 

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ፅ/ቤት

ስልክ ቁጥር 0111571847/0915747077

አዲስ አበባ 

ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርሲቲ 

Category:
Machinery and Equipment, Poultry, Bee and Animal Husbandry

Company Name:
Oda Buletum University

Company Amharic:
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

Posted Date:
Hidar 30, 2013

Opening Date:
Dec 24, 2020 02:30 PM

Ending Date:
Dec 24, 2020 02:00 PM

Newspaper:
Addis Zemen

Newspaper Publish Date:
Addis Zemen Hidar 30, 2013

Publish Date:
Hidar 30, 2013

Company image
<img style="height:50px;width:50px;border-radius:50%;" src="https://tender.awashtenders.com /img/companies/palceholder.png?1556635970″/>

Phones
[‘+251 255510878/1606/1610’, ‘+251 255510182 ‘]

Bid document price
150.00 ብር

Bid Bond
20,000.00 ብር