Ministry of Defense Peace Keeping Coordination Center

Addis Zemen Hidar 10, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ገ/ጨ/003/2013

ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ኢፌዲሪ መከላከያ ሚ/ር በሰላም ማስከበር ማዕከል በድሬዳዋ አካባቢ የሚገኘው ሁርሶ ኮንቲጀት ማት/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የማስልጠኛ ት/ቤታችንን የመኖሪያ ቤቶ ከፊል ዕድሳትና ጥገና ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማሰልጠኛ ት/ቤቱ ለስልጠና ምቹ እንዲሆኜ ምቹ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በዚህ ሥራ(የዕድሳትና የጥገና) ሥራ ለመሥራት ስለሚፈልግ በዚህ የግንባታ ሥራ ዘርፍ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የሚሰሩ ሥራዎችን ቦታው ላይ ሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት (ሁርሶ ካምፕ) ድረስ ተገኝተው ስራውን በአካል ማየት አለባቸው፡፡

የዕድሳትና ጥቼ ስራው ለዕድሳቱ የሚያስፈልጉ ሁሉንም እቃዎች ተጫራች የሚችል ይሆናል፡፡ የሚታደሱ የመኖሪያ ቤት ከፍሎች ብዛት 310 የሚታደሱ የሽንት ቤት ብዛት 186 የሚታደሱ የሻወር ቤት ብዛት 93 መስኮቶች በሮች እና አዲስ የሽንት ቤት ስራ ሌሎች ተዛማጅ ዝርዝር ስራዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙት ይሆናል፡፡

መመዘኛዎች፡ከላይ በየሎቱ (በየምድቡ) የተዘረዘሩትን የዕድሳትና ጥገና ሥራዎች የሚጠገኑበትንና የሚታደሱብትን ማቴሪያሎችችሎ በዘርፉ ለመስራት ብቃት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን መመዘኛ የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መሳተፍና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ማሰልጠኛት/ቤቱ በደስታ ይጋብዛል፡፡

 1. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
 2. በዘርፉ የተሰማሩበት የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ቲን ነምበር፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ በሚወዳደሩበት ዘርፍ (የግንባታ ሥራዎች) ዕድሳትና የጥገና ሥራ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
 3. የጥራት ደረጃው ፣ የሥራ ደረጃ የሚገልፁ ማስረጃ እንዲሁም የሚሳተፍባቸው ሥራዎችና የተሰጠው ንግድ ፍቃድም ከዘርፉ ተዛማጅ መሆኑ በሰነዶች ጀርባ የተዘረዘሩና የተገለፁ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም በዚህ ዘርፍ ለመሣተፍና ለመወዳደር በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው ፍቃድ ማስረጃ ኦርጅናልና ኮፒው ማቅረብ የሚችል ኦርጅናሉ ተመሳክሮ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ 50,000 ብር በባንክ ከተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሰሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች (በዚህ ዘርፍ) የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በማንኛውም ዕዳ ያልተያዘና ያልከሰሩ ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ያላቋረጡ ከንግድ ሥራ ያልታገዱ መሆን አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን 25/03/2013 ዓም ከሰኞ – አርብ በስራ ሰዓት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት በድሬዳዋና ዙርያው የምትገኙተጫራቶች በሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት ፋይናንስ ዴስክ ገንዘብ በመክፈል ከግዥ ዴስክ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛትና መውሰድ ይችላሉ። እንዲሁም በአ/አበባና ዙርያው የምትገኙ ጃን ሜዳ በሚገኘው የሠላም ማስከበር ማዕከል ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ በመከፈልና ሰነዱን ከግዥ ቡድን ቢሮ በመሄድ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።
 7. የጨረታ ሰነድ ሳጥን ከታሸገ (ከተዘጋ) በኋላ ዘግይተው የሚመጡ (የሚቀርቡ) መወዳዳርያ ሰነዶች በግዥ ህግ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደርያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ጀምሮ በተከታታይ ባሉ ለ15 ቀናት በሚወዳደሩበት ዘርፍ (የሥራ ምድብ) በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማት/ቤት ሁርሶ ግቢ ድረስ በአካል በመምጣት በማየት ጥናት በማድረግና ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይችላሉ፡፡
 9. የጨረታ መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
 10. ተጫራቾች ዋጋ የሚሞሉት በራሳቸው የተዘጋጀ ሰነድና (ፕሮፎርማ) ሆኖ ፊርማና ማህተም ያረፈበት እንዲሁም ለስንት ቀን እንደሚፀና መገለፅ አለበት፡፡
 11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 25/03/2013 ዓ/ም ነው፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቦታው ሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት (ሁርሶ ካምፕ) ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 19 ትንሹ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
 12. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ7 የሥራ ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ማሰርና መፈፀም አለበት፡፡
 13. በአንድ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
 14. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ መ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም፡፡
 15. ተወዳዳሪዎች በሚሰሩት ስራ ዘርፍ የደረጃቸው መግለጫና ማስረጃዎች ማቅረብ (መግለፅ) አለባቸው፡፡
 16. ማንኛውም ዶክመንት ኮፒ የሚደረጉ የሚነበቡና የሚታዩ መሆን አለበት፡፡
 17. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የተነካ መሆን የለበትም፡፡ እነዚህ ያለው ተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል። ምናልባት በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ስርዝ አድርጎ ስለ መሰረዙ ፊርማና ስሙን ማስቀመጥ አለበት፡፡
 18. አጠቃላይ አፈፃፀሙ የስምምነት ውላችን የሚካተት ይሆናል፡፡
 19. ማሰልጠኛ ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
 20. ለተጨማሪ መረጃ የማስታወቂያ ሽፋን በቀን 10/03/2013 ዓ/ም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቀርቧል፡፡
 21. ስለ ጨረታው ወይም ስለ ሥራው ማብራሪያ ከፈለጉ በሠላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰ/ት/ቤት ሁርሶ ከድሬዳዋ 27 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኝ ማሰልጠኛ ነው፡፡

በሰላም ማስበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሁርሶ ስ/ቁጥር፡- 0254470115 በመደወል መረጃ (ኢንፎርሜሽን) ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚ/ር ሰላም ማስከበር ማዕከል