Adet City Administration Finance and Economic Development Office

Be'kur መስከረም18፣2013

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የአዴት ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ ትብብር ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተሮች አገልግሎት የሚውል የእቃ ግዥ ለመፈጸም ሲሆን የሚፈለጉ ግዥዎች ዝርዝር፡-

ለእቃ ግዥ፡-

 • 1-ፈርኒቸር/የቤትና የቢሮ ዕቃዎች/ ግዥ
 • ሎት-1 ፣ 2- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
 • ሎት –2፣ 3- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
 • ሎት –3፣ 4-የመንገድ ዳር መብራት /ባዉዛ/ package no Adet-UIIDP-CW-04/20/20/20/20-ሎት-1 ሲሆን

ለግንባታ ግዥ፡-

 • 4-ተፋሰስ ግንባታ ከቻሌ ዘለቀ ቤት እስከ ወፍጮ ቤት ርዝመት 448 ሜትር package no Adet-UIIDP-CW-05/20/21-
 • ሎት-3፣ 5- ተፋሰስ ግንባታ ከአስማረ መንግስቱ ቤት እስከ ጋፋት ት/ቤት ርዝመት 230 ሜትር package no Adet-UIIDP-CW- 05/20/21-ሎት-1 ፣ 6- ተፋሰስ ግንባታ ከሙሉልብስ ቤት እስከ ሙላት ታደሰ ቤት ርዝመት 50 ሜትር package no Adet-UIIDP-CW-05/20/21-
 • ሎት-2፣ 7-የድሃ ድሃ ቤት ግንባታ አዴት ከ/አስ//04 ቀበሌ ጽ/ቤት አካባቢ package no Adet-UIIDP-CW-09/20/20/20/21
 • ሎት-1፣ 8- የባልትና ሸድ ግንባታ ቀበሌ 04 ጌሾ ገበያ ላይ package no Adet-UIIDP-CW 10/20/20/20/21 ሎት-1፣ 9-ቀበሌ 03 ከጋፋት ት/ቤት እስከ ሚካኤል ቤተክርስቲያን 0.02 ኪ/ሜ ገደል በጋቢወን የማሰር ስራ package no Adet-UIIDP-CW 06//20/21
 • ሎት-1፣ 10-ቀበሌ 05 ከጎሸየ መንገድ እስከ ቢተዉ ይብሩ ቤት0.02 ኪ/ሜ ገደል በጋቢወን የማሰር ስራ package no Adet-UIIDP-CW 06/20/21
 • ሎት-1፣ የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ስንጋብዝ ተፈላጊ መረጃዎች፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ ያላት ፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፣
 3. የግዥዉ መጠን ለግንባታ ከ50,000/ሃምሳ ሽህ/ ለእቃና አገልግሎት ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 5. የእቃው ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል መሆኑን፡፡
 7. ተጫራቾች የማይመለስ 50 ብር (ሃምሣ ብር) ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/
 • ፈርኒቸር/ለቤትና ለቢሮ እቃዎች/ ብር 9000/ዘጠኝ ሽህ ብር/
 • የጽህፈት መሳሪያ ብር 26000/ሃያ ስድስት ሽህ ብር/
 • ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎጭ ብር 8000/ስምንት ሽህ ብር/
 • የመንገድ ዳር መብራት /ባዉዛ/ ለሎት 1 ብር 7000 /ሰባት ሽህ ብር/
 • ተፋሰስ ግንባታ ከቻሌ ዘለቀ ቤት እስከ ወፍጮ ቤት ርዝመት 448 ሜትር ብር ለሎት 3 ብር /28000/ሃያ ስምንት ሺህ ብር/
 •  ተፋሰስ ግንባታ ከአስማረ መንግስቱ ቤት እስከ ጋፋት ት/ቤት ርዝመት 230 ሜትር ለሎት 1 ብር /15000/ አስራ አምስት ሺህ ብር/
 •  ተፋሰስ ግንባታ ከሙሉልብስ ቤት እስከ ሙላት ታደሰ ቤት ርዝመት 50 ሜትር ለሎት 2 ብር /3000 /ሶሰት ሺህ ብር/
 • የድሃ ድሃ ቤት ግንባታ ለሎት 1 ብር /14000 /አስራ አራት ሺህ ብር/
 • የባልትና ሸድ ግንባታ ለሎት 1 ብር /19000 /አስራ ዘጠኝ ሸህ ብር/
 • ቀበሌ 03 0.02 ኪ/ሜ ገደል በጋቢወን የማሰር ስራ ሎት-1 ብር 9000/ዘጠኝ ሽህ/
 • ቀበሌ 05 0.02 ኪ/ሜ ገደል በጋቢወን የማሰር ስራ ሎት- 2 ብር 9000/ዘጠኝ ሽህ/ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነትና ሎት በመፃፍ ከአዴት ከተማ አስ /ገን/አካ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 ለጫራታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡

10. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሰርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ከሆነ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለእቃ 15 ቀን ሆኖ በ16ኛው ቀን ለግንባታ 30 ቀን ሆኖ በ31ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በ16ኛው እና በ31ኛዉ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በአዴት ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል (እሁድ ቅዳሜ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል)፡፡

12. አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ወይም ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፡፡ ዋጋ ለይቶ መሙላት አይቻልም፡፡

13. የሚቀርቡት እቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆኑ በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ /ባለሙያ/ ተረጋግጦ ገቢ የሚሆን መሆኑና ልዮ ሙያ የሚጠይቅ ከሆነ በቴክኒካል ባለሙያዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

14. ጽ/ቤቱ እንደሁኔታው አይቶ የሎት ግዡን ለእቃ 20 በመቶ የመቀነስ የመጨር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. አሸናፊው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 3 ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 338 00 43 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

18. በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ማሣሰቢያ፡- ሌሎች ያልተጠቃለሉ ህጎችና መመሪያዎች በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ በተጨማሪ እኛ ከሸጥንላችሁ ሰነድ ውጭ በራሣችሁ ቅጽ መሙላት ፣በፍሉድ ማጥፋት፣ ስርዝ ድልዝ፣በራስ እስፔስፍኬሽን ዋጋ መሙላት እና ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

አዴት ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን