• Amhara

ANRS Area Forest and Wildlife Protection and Development Authority

Be'kur Tahsas 26, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

አብክመ አካባቢ ደን ዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን የሕብረት ሥራ ማሕበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እና የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሀማ አካላት ኤጀነሲ ለ2013 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ

 • የጽሕፈት መሳሪያ፣
 • ፈርኒቸር፣
 • ኤሌክትሮኒክስና
 • የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛትይፈልጋል::

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችል ይጋብዛል::

 1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመኾናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
 2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
 3.  የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የተርን ኦቨር ታክስ (TOT) ወይም በደረጃ ሐ ግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ ከኾኑ መመዝገባቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 4.  የሚሰጠው በተወካይ ከኾነ ደግሞ በበጀት ዓመቱ የታደሰ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መኾን ይኖርበታል::
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በኹኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኾነ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው::
 6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ::
 7. ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
 8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል አካባቢ ደን ዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ::
 9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የእቃ ዓይነት የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ 16ኛው ቀን ፡300 በመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 14 አጠገብ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲገባ መደረግ አለበት:: ጨረታው በዚያን ቀን 3፡30 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል::
 10.  ከ200 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ለኾኑ የቫት ተመዝጋቢ መኾን አለባቸው::
 11. ቫት ተመዝጋቢ ያልኾኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መኾን አለበት::
 12. ከ20 ሺህ ብር በላይ ላሉ ግዥዎች ቫቱን ቢሮው የሚያስቀር መኾኑን ይታወቅ::
 13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አካባቢ ደን ዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 6206 በመደወል መረጃው ማግኘት ይቻላል::

አካባቢ ደን ዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን