Akaki Kaliti Sub City Woreda 02 Administration FEDB

Addis Zemen ጥቅምት23፣2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ ለ2013 በጀት አመት በስሩ ለሚገኙት ለተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ለመግዛት በጨረታ ቁጥር፡ 01/2013  የወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ፡

 • ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር-2500.00
 • ሎት 2-የጽዳት ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር-2700.00
 • ሎት 3-የደንብ ልብሶች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር– 2300.00
 • ሎት 4-ቋሚ ዕቃዎች(ፈርኒቸር፤ኮምፒውተር፤ ላፕቶፖች የጋራ ጠረጴዛ እና ሌሎች) የጨረታ ማስከበሪያ ብር-1300.00
 •  ሎት 5- የደንብ ልብስ ማሰፊያ አገልግሎት—– የጨረታ ማስከበሪያ ብር-200.00 ሲሆኑ

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡

 1. በመጀመሪያ ደረጃ ሰነዱን መግዛት የሚችሉት፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የንግድ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ቲን ነምበር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል፣
 2. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ህግ ስለሙስና እና ጉቦ በተደነገገው መሰረት ሕጉን በማክበር ሁኔታን ለመፈፀም ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፣
 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት አገልግሎት/የዕቃውን ዓይነት፣ ስም፣ የተመረተበት ሀገር፣የሞዴሉን ቁጥር፣ የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገበዋል፣
 4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና የስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፣
 5. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ከየዓይነቱ አንዳንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን አይመለስም፣
 6. ጨረታው በቀኑና ሰዓቱ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
 7. ግዥ ፈፃሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር ይቻላል፣
 8. የጨረታው ማስከበሪያ በሎት በተጠየቀው መሠረት በሲፒኦ (CPO) ዋስትና በወረዳ 02 አስተዳደር /ቤት Woreda 02 Administration office/ በሚል በማሰራት በዋናው ወይም በኦሪጅናል ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፤
 9. ጨረታው በሁለት ኢንቨሎፖች የሚቀርብ ሆኖ በሰም መታሸግ አለባቸው፣በኢንቨሎፖቹ ዋና እና ፎቶ ኮፒ በመለየት የጨረታው ሰነድ መቅረብ አለባቸው፣ እነዚህም ሰነዶች በጨረታው ሲቀርቡ ድርጅቶቹ ወይም ህጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው፣ በሰነዶቹ እና ፖስታዎቹ ላይ የድርጅቱ/አቅራቢው ማህተም መኖር ይገባል፣
 10. የጨረታው ሰነዱ በራሱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይገባቸዋል፣
 11.  ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታው ሰነድ 70.00 ብር (ሰባ ብር) ከወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ቢሮ ቁጥር 203 2 ፎቅ በመግዛት መጫረት ይችላል፣
 12. የተሞላውን ሰነድ እስከ 11ኛው ቀን 400 ሰዓት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን 2 ፎቅ በሚገኘው ለዚሁ የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፤
 13.  ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 2 ህዳሴ አዳራሽ 4 ፎቅ የጨረታ ኮሚቴ ባለበት ይከፈታል፣ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
 14. የጨረታ አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርበታል፣
 15. የወረዳ 2 አስተዳደር /ቤት ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 16.  ክፍያን በተመለከተ አቅራቢው ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በጥራት እና በናሙና መሠረት በቴክኒክ ኮሚቴ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን የሚከፈል ይሆናል፣
 17.  አሽናፊዎች ባሸነፉት ዕቃዎች ከጠቅላላው ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበቸዋል፣
 18. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታው ሰነድ የመክፈቻ ጊዜ አምስት ቀን እስከሚቀረው ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፣
 19. ተጫራቾች በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላል፣

አድራሻ፡አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ አቃቂ ቆርቆር ፋብሪካ አካባቢ

የወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ይገኛል፤

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0114351914/0114715165 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ /ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 ፋይናንስ /ቤት