National Oil Ethiopia

Addis Zemen መስከረም15፣2013

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ቃሊቲ ዴፖ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ብዛት ያላቸውን ዘይትና ኩላንት ያሉባቸው መያዣቸው የተበሳ/የተቀደደ በርሜሎች፣ጀሪካኖችና ትንንሽ መያዣ ያላቸው እቃዎች ሲሆን እቃዎችም፡

  • በበርሜል፡የተበሳ/ የተቀደደ 47,Slow moving/አዝጋሚ እንቅስቃሴ ያላቸው 1457 የተበሳ/ የተቀደደ ጀሪካኖች 778 የተበሳ/የተቀደደ ትንንሽ መያዣ ያላቸው 285 ናቸው በመሆኑም፡ ዘይቶቹን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ለእያንዳንዳቸው ለተጠቀሱ እቃዎች ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይቻላል። እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦታው ላይ በመመልከት እያንዳንዱን የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪ ብር 15,000.00 ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል፡፡

አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለጸለት ገንዘቡን በአንድ ከፍያ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ይህን ባይፈጸም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ አሸናፊ እቃዎቹን በአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ከቃሊቲ ዴፖ ማንሳት አለበት ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 500.00 ብር ይከፍላል፡፡ ሙሉ ክፍያ ፈጽም ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል፡፡

ድርጅቱ የተሻለመንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ(ኖክ)