Bonga University

Addis Zemen Tahsas 30, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2013/

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

 1. ሎት-01 ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆን ቅመማ ቅመም ግዥ
 2. ሎት-02 ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆኑ የተለያዩ የምግብ ሰብልና ጥራጥሬ ግዥ
 3. ሎት-03 : ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆኑ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ግዥ
 4. ሎት-04 ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆን የከብት ስጋ ግዥ
 5. ሎት-05 ለተማሪዎች ቀለብ የሚሆን የዳቦ ዱቄት እና የምግብ ዘይት ግዥ
 6. ሎት-06 የምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ እቃዎች /kitchen materials/ ግዥ
 7. ሎት-07 የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ
 8. ሎት– 08ለተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ወንበር፣ ጠረጴዛዎች እና ለሌሎች ተጓዳኝ እቃዎች Furnitures/ ግዥ
 9. ሎት-09 የህዝብ ማመላለሻ መኪና አገልግሎት ግዥ
 10. ሎት-10 የተለያዩ የውሃ እቃዎች ግዥ
 11. ሎት-11 መድሃኒትና የመድሃኒት መገልገያ እቃዎች ግዥ

በዚሁ መሠረት፡-

 1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
 3. የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (Tin No) ያላቸው
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
 5. በመንግስት ግዥ ሰአቅራቢነት የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 6. በማንኛውም የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ
 7. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት– 01, ሎት– 02,ሎት– 03, ሎት– 04 እና ሎት– 05, 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር እንዲሁም ለሎት-06,ሎት-07, ሎት-08,ሎት-09.ሎት-10, እናሎት11 ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /BID-BOND/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማህበራት ለጨረታ ማስከበሪያ  ከአደራጁ መ/ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ  የተቀመጠው የገንዘብ መጠን ተገልጾ በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲው የተፃፈ ኦርጅናል የዋስትና ደብዳቤ ካልቀረበ ተቀባይነት የለውም ወይም እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 8.  በሁሉም ሎቶች ያሸነፏቸውን እቃዎች ያለ ምንም ቅድመክፍያ ዩኒቨርሲቲው በሚፈልገው ብዛት ጠቅላላ ዋጋ 10% /አስር ከመቶ/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት የሚችልና እቃዎችን ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆኑ፣
 9. በሁሉም ሎቶች ያሸነፏቸውን እቃዎች እስከ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በራሱ ሙሉ ወጪ እና ትራንስፖርት በማጓጓዝ ለማስረከብ እንዲሁም እንደየእቃዎቹ ባህሪይ ገጠማ እና ስልጠና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በተሟላ መልኩ ገጥመውና ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች የአጠቃቀም ስልጠና በመስጠት እቃዎቹ በዩኒቨርሲቲው የእቃ ጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ ጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ገቢ በማድረግ ከፍያ ለመቀበል ፍቃደኛ የሆኑና የሚችሉ
 10. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የባንክ ሂሳብ ጥር 1000177534513 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግና የባንከ ገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ /ሰነዶችን/ ከአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት የትም/መሳ/ማም/ድርጅት ጊቢ ውስጥ ከሚገኘው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለሚናር ህንፃ ግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፣
 11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ 16ኛው ቀን ልከ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ልክ ከጠዋቱ 430 ሰዓት በአዲስ  አበባ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ማስተባበሪያ /ቤት እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር  ሕንፃ 2ተኛ ፎቅ ሴኔት አዳራሽ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት  የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
 12.  ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓላትና ሌሎች ችግሮች ቢያጋጥሙ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 13. ተጫራቾች የጨረታውን መጫረቻ ዋጋ ሲሞሉ ከነ ቫት መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣
 14. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ /ሃሳብ/ ስዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ያለ ምንም ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፤ ከተሳሳቱ ከፊት ለፊት በፊርማቸው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል
 15. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአንድ ፖስታ ከአንድ ተጨማሪ ኮፒ ጋር በማዘጋጀት የድርጅቱን ሙሉ ስምና አድራሻ እንዲሁም ማህተም በፖስታ ላይ እና በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ በማሳረፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ አሽገው የኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 17.  የጨረታ ሰነድን አስመልክቶ ማንኛውንም ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻለው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
 18. የጨረታ ውጤትን አስመልክቶ ማንኛውንም ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (7) ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡
 19. ለአሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሊመለስ የሚችለው ውል ፈጽመው የውል ማስከበሪያ ካስያዙ ብቻ ሆኖ ውል ለመፈጸም ፍቃደኛ ካልሆኑ በግዥ አዋጅ እና የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፣
 20. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ሃሳብ መሙያ ፎርም ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ የድርጅቱ ባለቤት ተወካይ ስም እና ፊርማ በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
 21. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ነገር ግን በእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ሰነድ/ ላይ የተካተቱ ዝርዝር ሀሳቦች በዚህ ጋዜጣ ላይ እንደተገለጸ ይቆጠራል፡፡
 22.  ተጫራቾች ለሞሉት ዋጋ ሃሳብ/ መሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡
 23. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 4524588 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ