Federal House Corporation Liyu Branch

Addis Zemen Tahsas 15, 2013

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር // 01/2013

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ /ቤት አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉና

 • አዳዲስ የቢሮ እቃዎች፣
 • የግንባታ እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡

 1. ለገሀር በሚገኘው በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ /ቤት ቢሮ ቁጥር 004 በመምጣት በቅርንጫፉ ሥር በሚገኙ አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉና አዳዲስ የቢሮ እቃዎች፣ የግንባታ እና የተለያዩ እቃዎችን ዝርዝር የያዘውን መረጃ ፣የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
 2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሁም የንብረቱን ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ በማሣየት ድምሩን በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በልዩ ቅርንጫፍ /ቤት የፋይናንስ ገቢ አሰባሰብ ቡድን ቢሮ ቁጥር 004 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ በየምድቡ ከተቀመጡት እቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን እቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም፤
 3. የእቃው /ንብረቱ ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ ዋጋው ፣የተጨማሪ እሴት ታክሱና ጠቅላላ ድምሩ በሠንጠረዥ መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
 5. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
 6. ተጫራቾች ለሚገዙት የቢሮ፣ የግንባታ እና የተለያዩ እቃዎች ላይ በጥቅል 8,000.00/ስምንት ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫ ፎቶ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
 7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ቅርንጫፍ /ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ሲቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
 8. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
 9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
 10. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፤
 11. ተጫራቾች የጨረታው ውጤቱ በልዩ ቅርንጫፍ /ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 12. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል።
 13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል እቃዎቹን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የእቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001%/1/1000/ በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለቅርጫፉ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል፤
 14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 011-5-154905 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
 15. ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት፤
 16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የልዩ ቅርንጫፍ /ቤት