• Wollo

FDRE Private organizations Employees Social Security Agency

Addis Zemen Tir 22, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የኢፌዴሪ የግል ድርጅቻ ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የሰሜን ምስራቅ  ሪጅን ፅ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት አስፈላጊ የሆኑ የቢሮ እቃዎች

ማለትም፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣

 • ቋሚ እቃዎች፣
 • ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣
 • ደንብ ልብስ እንዲሁም
 • የፅህፈትና
 • የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፣

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫሪቶች ባለሙያ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ መሆኑ
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 
 3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው!
 4. የግዥው መጠን ከብር 100,000,00 ከአንድ መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
 6. የሚገዙ እቃዎችን እይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤ ነገር ግን ሰነዱን መሙላት  ያለባቸው ከነቫቱ ነው፡፡ መ/ቤቱ ቫት ሰብሳቢ መሆኑም ከወዲሁ መታወቅ አለበት ::
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከግዥ እፈሰር ቢሮ ማግኘት ይችላሉ!
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ቢድ ቦንድ /Bid bond/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
 9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 10. ተጫራቾች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ መሰረት የሚያቀርቡት እቃ ትከከለኛ መሆን አለበት፡፡
 11. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላትና እስፈላጊ ዶክመንቶችን በሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና ኦሪጂናል/ እና ኮፒ በማለት በማዘጋጀት እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም እድርጎ በማሸግ በጽ/ቤቱ የሰው ሀብት አቅርቦትና ጠቅላላ አገልግሎት የስራ ሂደት በግዥ ባለሙያዎች ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ ይቆይና በዕለቱ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ፅ/ቤት  ኮምቦልቻ የግዥ ስራ ክፍል ይከፈታል፡፡
 13. ተጫራቾች ላሸነፉበት እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 14. የጨረታው መዝጊያጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችልም፡፡
 15. በጨረታው ተወዳድረው ሲያሸንፉ እቃውን ማሽነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እጅግ ሲዘገይ በ15 ቀናት ውስጥ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉት በስቶክ ውስጥ ከምችት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስግዥ የስራ ክፍል በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335510776 /033-551-36-48 /033-551-4533 / በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 17.  ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም መ/ቤቱ የቫት ሰብሳቢ መሆኑን ተጫራቾች እንዲያውቁ በድጋሚ እናሳውቃለን፡፡

አድራሻ፡- ኮምቦልቻ ከተማ /ደቡብ ወሎ/ ቀበሌ 05 ከማረሚያ ቤት ጀርባ ኣማራ ብድርና ቁጠባ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ነው፡፡

በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና

ኤጀንሲ የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ፅ/ቤት