• Gedeo

Gedio Zone FEDB

በ15ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት

ግልፅ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በጌዴኦ ዞን ፋይ/ኢኮ//መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ የሆነው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ 2012 በጀት ዓመት በቡሌ ወረዳ አዳዶ ቀበሌ በሚያስገነባው የጤና ጣቢያ ግንባታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ተቋራጮች ማሟላት ያሉባቸው መመዘኛዎች:

 1. BC/GC/ በደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ፤
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ 2012 / የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin Number/ያለውና ማቅረብ የሚችሉ
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
 6. ከመንግሥት የሚፈለግበትን የግብርና የታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል፤ የስምምነት ደብዳቤ ከገቢዎች /ቤት ማቅረብ የሚችሉ
 7. በዞናችን የግንባታ ውለታ ገብተው ባላቸው ደካማ አፈጻጸም የተነሳ ውለታ ያልተቋረጠባቸው እና ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው
 8. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮችን እየጋበዝን ከተራቁጥር 1-8 የተጠቀሱ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር ብቻ በፕሮጀክቱ ስም በጌዴኦ ዞን ገቢዎች //ቤት ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናልና ኮፒውን በማቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሰነድ ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶቻቸውን በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፈርማ በማሳረፍ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ኮፒ ሰነድ በፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ የተደረጉ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በማሸግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ድረስ በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  • በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ መፈረም ይኖርበታል፤
  • ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ  ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም::
  • በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል፣
  • ጨረታው የሚዘጋው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን 430 ሰዓት በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ይሆናል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ሳያሟላ የሚያቀርብ ተቋራጭ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል። ጨረታው የሚገመገመው የደቡብ //// እንደገና ተሻሽሎ በወጣ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 28/2010 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነው
  • /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0461310108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

በጌዲኦ ዞን ፋይ/ኢኮ//መምሪያ

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት