Jimma Zone Omo Biyem Woreda Road Authority

Addis Zemen Dec6,2020

የጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ መንገዶች ባለሥልጣን /ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚያሠራው ሶምቦ በዳላ ኮዳ መንገድ ማሽኖችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ የወረዳው መንገዶች ባለሥልጣን /ቤት በሚያወጣው የጨረታ መስፈርት እና ደንብ መሠረት መጥታችሁ መወዳደር የምችትሉ መሆኑን እገገልጻለን፡፡

ተ.ቁ

የማሽነሪው ዓይነት

ብዛት

የስሪት ዘመን እኤአ

1

ዶዘር D8R CAT

1

2007-ወዲህ

በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቁ መስፈርቶች፡

 1. የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን የማከራየት ፍቃድ ያላቸው፣
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና TIN ቁጥር ያላቸው፣
 3. 2012 . የመንግሥት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ፣
 4. ከሥራ እና ከተማ ልማት የተሰጣቸውን የታደሰ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. አዳዲስ ማሽኖች ተመራጭነት አላቸው፣
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለሥልጣን /ቤት ቀርበው የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( Bid bond) የጠቅላላ ዋጋን 2% በክፍያ ማረጋገጫ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ተጫራቾች የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል ዶክመንት በጥንቃቄ በመሙላት እና አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማያያዝ ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ሁለቱንም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሁለቱንም በሦስተኛ ኤንቨሎፕ በማሸግ እና ቴከኒካል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
 9.  የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል) ዶክመንት ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ በፖስታ ለየብቻ በሰም በማሸግ ተገቢውን መረጃ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለየብቻ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሦስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በመጨረሻም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ተፈላጊውን መረጃ በጉልህ ግልፅ በሆኑ ጽሑፍ በመጻፍ መግባት አለበት፡፡ 
 10.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 600 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ አስተዳደር /ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡
 11. ስርዝ ድልዝ ያለባቸውንና በግልፅ የማይነበቡ አሻሚ ፊደሎችና ቁጥሮች ያላቸው ሰነዶች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ማሳሰቢያ፡/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ኦሞ ቤየም ወረዳ ከፊንፊኔ 326 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡– 0917234760 አልያም በወረዳው መንገዶች ባለሥልጣን /ቤት በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ መንገዶች ባለሥልጣን /ቤት