• Gondar

Sede Muja FEDB

Be'kur Tir 17, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ጎንደር አስ/ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ የገ/ኢ/ል/ት/ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት  የሚውል

 • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ፣
 • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ፣
 • ሎት 3 ደንብ ልብስ ፣
 • ሎት 4 ፈርኒቸር ፣
 • ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ፣
 • ሎት 6 የመኪና ጎማ እና
 • ሎት 7 ህትመት በ2013 በጀት ዓመት መግዛት ስለሚፈልግ በግልፅ ጨረታ እንዲወጣለት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ መወዳደር ይችላል፡፡
 1. በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
 2. የዘመኑን ግብር የከፈለና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችል፣
 3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200 ሽህ /ሁለት መቶ ሽህ / ብር እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
 4. የመልካም ስራ አፈፃፀም መገለጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
 5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) ለእያንዳንዳቸዉ በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ቀን መግዛት ይችላሉ፣
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1 በመቶ (አንድ በመቶ ) በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና ሌሎች መረጃቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታዋቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚታሸግበት ቀን እና ስዓት ድረስ በሰዴ ሙጃ ወረዳ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለስራው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፣
 8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት በግ/ን/አስ/ቢሮ ይከፈታል፣
 9. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፣
 10.  የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
 11.  ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻለን፣
 12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 13. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
 14. ጨረታውን ለመክፈት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ለመክፈት አያስተጓጉልም ፣
 15. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተቀመጠዉ ስዓት ይሆናል፣
 16. ለበለጠ ማብራሪያ በሰ/ሙ/ወ/ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 በአካል ቀርበው ጠይቆ ወይም በስልክ ቁጥር 058 140 10 76 ደዉሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የሰ/ሙ/ወ/ገ/ኢ/ል ዋና ፅ/ቤት