Gedio Zone Sustainable Development Project Bureau

Addis Zemen Tahsas 20, 2013

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የጌዴኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት በዞኑ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ፕሮጀክቶችን ለመገንባትና ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን፣ ጉልበትና መሳሪያዎችን አቅርበው የሚሰሩ ብቁ የግንባታ ተቋራጮችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ

የጨረታ ሠነድ (LOT)

ፕሮጀክት

የሚገነባበት ቦታ

የተቋራጭ ደረጃ

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

የጨረታ ሰነድ ዋጋ

ምርመራ

 

1

Lot 1/2013

B+G+5 የዞን አስተዳደር ሕንጻ፣ ዘመናዊ አዳራሽ፣ ሁለት ብሎክ G+1 የባህል ማዕከል እና የጌዴኦ ብሔር ባህላዊና የጀግንነት ሥነ – ሐውልት

ዲላ ከተማ

GC/BC

500,000

3000

አዲስ

2

Lot 2/2013

G+2 የፖሊስ መምሪያ ቢሮ

ዲላ ከተማ

BC-3/GC-4 እና ከዚያ በላይ

150,000

1000

በጅምር ላይ የሚገኝ

3

Lot 3/2013

G+2 የትምህርት እና የፐብሊክ ሰርቪስ መምሪያ ቢሮ

ዲላ ከተማ

BC-3/GC-4 እና ከዚያ በላይ

150,000

1000

በጅምር ላይ የሚገኝ

4

Lot 4/2013

ሁለት ብሎክ G+1 መማሪያ ክፍል እና የአስተዳደር ብሎክ ያካተተ ጩምቡሮ ሹንዴ ምችሌ መታሰቢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ምችሌ ሲሶታ ዲላ ዙሪያ ወረዳ

BC-5/ GC-6 እና ከዚያ በላይ

 

100,000

500

አዲስ

 

በዚህም መሠረት፡-

 1. የግብር መለያ ቁጥር ያለው፣ በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና ለ203 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፤
 2. የግብርና የታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገለጽ የስምምነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
 3. የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች ባለሥልጣን የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
 4. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር (Suppliers List) ውስጥ የተመዘገበ ስለመሆኑ የምዝገባ ምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
 5. የመልካም ሥራ አፈጻፀም የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮችን እየጋበዘ ከላይ የተጠቀሱ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ ብር 3000 /ሦስት ሺህ ብር/ ለሎት አንድ Lot 1, 1,000 /አንድ ሺህ ብር /ለሎት ሁለት Lot 2 ፣ 1,000 (አንድ ሺህ ብር/ ለሎት ሦስት Lot 3/ እና 500 /አምስት መቶ ብር/ ለሎት አራት Lot 4/ በፕሮጀክቱ ስም በጌዴኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕ/ፅ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብ/አስ/የሥራ ክፍል ገቢ በማድረግ እና ደረሠኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ኮፒ ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሠነድ ከጌዴኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
 • ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናንሻል የጨረታ ሠነዶቻቸውን ለየብቻ በማድረግ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማሣረፍ እያንዳንዳቸውን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሠነድ በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ስእናት ፖስታ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በጌዴኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕ/ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • በኦርጅናል ሠነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ሥርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርባቸዋል። ሥርዝ ድልዝ የማይነበብ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል/፡፡
 • እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር ለLOT 1, ብር 150,000 / አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ ለLOT 2, ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር ለ LOT 3 ፣ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር / ለLOT 4 / በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፤ (ሲፒኦ በተናጠል ፖስታ በሰም መታሸግ አለበት።
 • በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሠነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
 • የጨረታው ሣጥን መዝጊያና መከፈቻ እንደየሎቱ የሚለያይ ሲሆን ሎት1 በ45ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ ሎት 2 በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ ሎት 3 በ21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ሎት 4 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና የሚመለከታቸው ከፍሎች በተገኙበት በጌዴኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ 
 • ከላይ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ሳያሟሉ የሚቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
 • ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ተጫራቾች ማንኛውንም የጨረታ ሠነድ ሙግዛት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን አንድ ሠነድ ብቻ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ተጫራች ከጨረታው በቀጥታ ውድቅ ይሆናል፡፡
 • ቦታው ከዲላ ከተማ መናኸሪያ ወደ ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው ኢንተርናሽናል መንገድ ከጅብሪል ጋራዥ ጎን፤
 • ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡ 046131-93-66 / 046131-44-82

የጌዲኦ ዞን ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ፅ/ቤት የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ስ/ክፍል

ዲላ