Dasenech woreda Court Omorate

Addis Zemen Hidar 27, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ተጀምረው ሳይጠናቀቅ የተቋረጠውን የፍርድ ቤት ግንባታ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በተገለጸው መሰረት በ2013 የበጀት ዓመት ለማስገንባት ፦ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የግንባታው ዓይነት

የግንባታው ቦታ

የተጫራች ደረጃ

የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በ CPO ብቻ

1

ዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት

ኦሞራቴ

ጂሲ/ቢሲ ደረጃ ሰባትና ከዚያ በላይ

10,000 / አስር ሺህ / ብር

 

በዚህም መሠረት፡- 

 1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፤ በክልሉ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ ለ 2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከላይ በሠንጠረዥ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፡፡
 2. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና ለ 2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
 4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
 5. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታክስ ኪሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ Malid tax clearance certificate 
 6. በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Registered in PPPA or PPA Suppliers List /
 7. ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረከብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል ማዘግየት፣ ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈፃፀም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማንኛውም የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀከቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ ፤ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡
 8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የፅሁፍ ማመልከቻ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ከፍል የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
 9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ከታወቀ ባንከ በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ቴክኒካል ኦርጂናል ዶከመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
 10. ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴከኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሰላሳ አንደኛው /31ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡25 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በሰም አሽገው በሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ካኪ ፖስታ ላይ በጥንቃቄ አስፈላጊውን መረጃ መግለፅ አለባቸው፡፡ የጨረታው አከፋፈት በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶከመንት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፤

 • መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0909198826 ወይም 0916779112 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር

የዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት

ኦሞራ