Keffa Zone Gesha Woreda Administration Bureau

Addis Zemen Tir 9, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ደካ ማዘጋጃ ቤት ከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ጠረጋና ጠጠር ዝርጋታ ሥራ ለማሥፋፋት ፈልጎ ዶዘር፣ ግሬደርና ገልባጭ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሣውቃለን።

  • በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፤
  • የዘመኑን ግብር የከፈለና በወቅቱ የንግድ ፍቃድ ያሣደሰ፤
  • ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤
  • ለመንግሥት 2 በመቶ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፤

የሥራ ዝርዝሮች

  • ዶዘር ከነኦፕሬተርና ነዳጅ በማቅረብ መንገድ ከፈታና ጠረጋ ሥራ መሥራት በሰዓት፣
  • ግሬደር ከነኦፕሬተርና ነዳጅ በማቅረብ አፈር ጠረጋና ማቴሪያል መበተን ቦይ ማውጣት በሰዓት፣
  • ገልባጭ ከነሾፌር ነዳጅና ረዳት በማቅረብ በሜትር ኪዩብ መሥራት የሚችል፣

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማሥረጃዎች በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ ሀያ [20/ ቀናት ውስጥ በጌሻ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 ከፍል ተጫራቾች የማይመለስ 50 ብር በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ሥም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛ ተከታታይ ቀናት እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ አስ/ር ኬዝ ቲም ቢሮ በ 21ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም

ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን እያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ሠንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ 5000 በካሽ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝcPO በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተየባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ስልክ፤ 047-774-0329 / 047-774-0201

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሳ ወረዳ

ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት